የእንግሊዝ አግርኳስ ማህበር የዌምብሌ ስታድየምን ሊሸጠው ነው

የእንግሊዝ እግርኳስ ማህበር ታላላቅ ጨዋታዎችን በማስተናገድ የሚታወቀው የዌምብሌ ስታድየም ለመሸጥ በድርድር ላይ እንደሆነ ታውቋል።

የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን ጨዋታዎች እንዲሁም እንደ ኤፍ ኤ ካፕ አይነት የፍፃሜ ጨዋታዎችን እያስተናገደ ለረጅም አመት የቆየው የዌምብሌ ስታድየም በግል ባለሀብት እጅ ለመግባት ተቃርቧል።

5.2 ቢልየን ፓውንድ ሀብት እንዳላቸው እና በፎርብስ መፅሄት የሀብት ደረጃ ከአለም 217ኛ ደረጃ ላይ የሚገኙት የፉልሀም እና የአሜሪካው ጃግዋር ክለብ ባለቤት ሻሂድ ከሀን ከ 800 ሚ ፓውንድ በላይ በማውጣት ዊምብሌን ለመጠቅለል መቃረባቸው ተሰምቷል።

የእግርኳስ ማህበሩም ስታድየሙን ለመግዛት ይፋዊ ጥያቄ እንደደረሰው ያረጋገጠ ሲሆን ጥያቄውን ለመመልከት ለውይይት መቀመጡ ታውቋል። 

ዜናው በእንግሊዛዊያን ያልተወደደ ሲሆን የግዙፉ ስታድየም የስያሜ ጉዳይ እና የብሔራዊ ቡድናቸው የመጫወቻ ቦታ እንዳይነፈጉ ከወዲሁ ስጋት አድሮባቸዋል።

እንደ መረጃዎች ግን ሜዳው ለባለሀብቱ ተላልፎ ቢሰጥም እንኳን በሜዳው ላይ ሲደረጉ የነበሩ ታላላቅ ጨዋታዎች ግን በተመሳሳይ መደረጋቸውን እንደሚቀጥሉ ነው።

Advertisements