ስንብት/ ቪንሴንዞ ሞንቴላ ከሲቪያ ሀላፊነቱ ተሰናበተ

የአንዳሉሺያኑ ሲቪያ የክለቡን አሰልጣኝ ቪንሴንዞ ሞንቴላን ከሀላፊነታቸው ማንሳቱን ይፋ አድርጓል።

<!–more–>

ጣሊያናዊው አሰልጣኝ ቪንሴንዞ ሞንቴላ በአንድ አመት ውስጥ ለሁለተኛ ጊዜ ከሀላፊነቱ የተነሳ ሲሆን በምትኩ ጁአኪን ካፓሮስ የሲቪያ አሰልጣኝ ሆነው እስከ አመቱ መጨረሻ ድረስ ተሹሞዋል።

ሞንቴላ በቻምፕየንስ ሊጉ ማንችስተር ዩናይትድን ካሸነፈ በኋላ በሁሉም ውድድሮች ያደረገውን ዘጠኝ ጨዋታዎች ማሸነፍ አልቻለም።

በኮፓዴልሬ የፍፃሜ ጨዋታ ላይም ባለፈው ሳምንት በባርሴሎና 5-0 በሆነ ሰፊ ውጤት ተሸንፈዋል።

ከኤድዋርዶ ቤሪዞ ተረክቦ ላለፉት አራት ወራት ከአንዳሉሺያኑ ክለብ ጋር ቆይታ ያደረገው ሞንቴላ ቡድኑ ውጤት አልባ ጉዞ እያደረገ በመሆኑ ከክለቡ መሰናበቱ ታውቋል።

ክለቡ በላሊጋው ሰባተኛ ደረጃ ላይ የሚገኝ ሲሆን አዲሱ አሰልጣኝም ቡድኑ የዩሮፓ ሊግ ተሳትፎ አግኝቶ እንዲያጠናቅቅ ሀላፊነት እንደተሰጣቸው ታውቋል።

Advertisements