የቀድሞ የዋሊያዎቹ አሰልጣኝ የነበሩት ቶም ሴንትፌት ከማልታ ብሔራዊ ቡድን ሀላፊነታቸው ተሰናበቱ 

2011 ላይ ​የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንን ያሰለጠኑት ቤልጄማዊው ቶም ሴንትፌት ከማልታ ብሔራዊ ቡድን ሀላፊነታቸው ተሰናብተዋል።

አሰልጣኙ ከሀላፊነታቸው የተነሱት የካሜሮን ብሔራዊ ቡድንን ለማሰልጠን ማስረጃቸውን በማስገባታቸው እንደሆነ ታውቋል።

77 አሰልጣኞች ለካሜሮን ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝነት ያመለከቱ ሲሆን ከነዚህ ውስጥ ቶም ሴንትፌት አንዱ እንደሆኑ በሰፊው መረጃዎች ገልፀዋል።

ነገርግን እሳቸው እውነታ የሌለው መረጃ እንጂ የተናፈሰው ወሬ የተሳሳተ መሆኑን ተናግረዋል።”በተሳሳተ መረጃ ተጠቂ መሆኔም አዝኛለው።” ሲሉ ስሜታቸውን ገልፅዋል።

ቶም ሴንትፌት ጨምረው “ለካሜሮን ብሔራዊ ቡድን ወይንም ለሌላ የአሰልጣኝነት ቦታ ያመለከትኩት ነገር የለም።ይህንንም ለማልታ እግርኳስ ፌዴሬሽን ማስረጃ በማቅረብ አስረድቻለው

“የእውነት በተሰራጨው የሀሰት መረጃ ተከፍቻለው።ስለዚህ አሁን ጉዳዩን ለጠበቃዬ አሳልፌ ሰጥቻለው።”ሲሉ ተናግረዋል።

የማልታ እግር ኳስ ማህበር በመግለጫው “የተከሰተውን ሁኔታ በጥልቀት ከመረመርን በኋላ በቶም ሴንትፌት ቆይታ ላይ ውሳኔ ወስነናል።በዚህ ምክንያት ከብሔራዊ ቡድኑ ሀላፊነት ኮንታራታቸውን አቋርጠናል።”ሲሉ አሳውቋል ።

አሰልጣኙ ከማልታ ጋር ሶስት ጨዋታዎችን ብቻ ያደረጉ ሲሆን ምንም ጨዋታ ሳያሸንፉ ፣ሁሉንም ተሸንፈው 12 ጎል አስተናግደዋል።

ባደረጉት ጨዋታ ምንም አይነት ጎል ሳያስቆጥሩ ደካማ አጀማመር ማድረግ ችለዋል።

ቶም ሴንትፌት ባለፈው ጥቅምት ወር ላይ ፒትሮ ጌዲን ተክተው የማልታ ብሔራዊ ቡድንን ለማሰልጠን በሀላፊነት መረከባቸው ይታወሳል።

Advertisements