በሀምቡርግ ማራቶን ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች አሸናፊ ሆኑ

በጀርመን ሀምቡርግ የተካሄደው አመታዊ የማራቶን ውድድር በወንዶች ኢትዮጵያዊ አትሌቶች ተከታትለው ሲገቡ በሴቶች ሁለተኛ ደረጃ ይዘው አጠናቀዋል።

<!–more–>

42 ኪ ሜ የሚሸፍነው እና በወርሀ ሚያዚያ የሚካሄደው አመታዊው የሀምቡርግ ማራቶን ዛሬ ተከናውኗል።

በወንዶች እና በሴቶች በተካሄደው ውድድር ኢትዮጵያዊው ሰለሞን ዴክሲሳ በወንዶች አሸናፊ ሲሆን በሴቶች ደግሞ ለባህሬን እየተወዳደረች የሚገኘው ሽታዬ እሸቴ አሸንፋለች።

ሽታዬ እሸቴ

ሰለሞንን በመከተል ደግሞ ታዱ አባተ እና አየለ አብሽሮ ተከታትለው ሲገቡ በሴቶች ደግሞ ብርቄ ደበሌ ሁለተኛ ሆና አጠናቃለች።

ሰለሞን አሸናፊ የሆነበት ሰአት 2:06:34 በመግባት ሲሆን በሁለተኛ እና ሶስተኛ የወጡት ሌሎች የኢትዮጵያ ሯጮች የሆኑት ታዱ አባተ እና አየለ አብሽሮ 2:06:54 እንዲሁም 2:07:19 በሆነ ሰአት አጠናቀዋል።

በውድድሩ ላይ የኢትዮጵያ እና የኬኒያ አትሌቶች እየተፈራረቁ አሸናፊ በመሆን የሚታወቁ ሲሆን ባለፉት አመታት ግን ኢትዮጵያዊያን በተከታታይ ማሸነፍ ችለዋል።

የውድድሩ ፈጣኑ ሰአት ኤሪክ ኪፕቾንጌ 2013 ላይ አሸናፊ ሲሆን የገባበት ሰአት ሲሆን ይህም 2:05:30 ነው።

ባለፈው አመት ፀጋዬ መኮንን 2:07:26 በመግባት የውድድሩ አሸናፊ እንደነበር ይታወሳል።

Advertisements