ሊዬኔል ሜሲ የላሊጋ ክብረ ወሰን ማስመዝገብ ቻለ

Image result for messi

ፅሁፍ ዝግጅት ፦ መንሀጁል ሀያቲ

አርጀንቲናዊዬ ኮከብ ሊዬኔል ሜሲ ባርሴሎና ከዲፖርቲቮ ላካሮኒያ ጋር ባደረገው ጨዋታ ላይ ሊዬኔል ሜሲ የላሊጋ ክብረ ወሰን ማስመዝገብ ችሏል።

ባርሴሎና የላሊጋውን ዋንጫ ማንሳቱን ባረጋገጠበት ጨዋታ ላይ አርጀንቲናዊዬ የኳስ ምትሀተኛ ሌዬኔል አንድሪያስ ሜሲ ለተከታታይ 7 ሲዝኖች በላሊጋው 30 እና ከዛ በላይ ጎሎችን ማስቆጠር የቻለ ተጨዋች በመሆን አዲስ ሪከርድን ማስመዝገብ ችሏል።

ሜሲ ትላንት ምሽት ደምቆ ማምሸት የቻለ ሲሆን በጨዋታው ተጨማሪ ሀትሪክ በመስራት የካታሎኑ ክለብ የላሊጋውን ዋንጫ ማንሳቱን እንዲያረጋግጥ መርዳት ችሏል።

ምትሀተኛ መሲ ከዚህ በተጨማሪም የአውሮፓ ኮከብ ጎል አግቢነቱን ክብር ከግብፃዊዬ ሙሀመድ ሳላህ መረከብ የቻለ ሲሆን የኮከብ ጎል አስቆጣሪነቱን ክብር በ43 ጎሎች ሞ ሳላን እንዲሁም ክሪስቲያኖ ሮናልዶን በማስከተል በመምራት ላይ ይገኛል፡፡

 

Advertisements