ባርሴሎና ለ25ተኛ ጊዜ የላሊጋ ዋንጫን ማንሳቱን አረጋግጧል

ፅሁፍ ዝግጅት ፦ መንሀጁል ሀያቲ

ብሉግሪያንስ ለ25ተኛ ጊዜ የላሊጋውን ዋንጫ ወደ ካምፕ ኑ መውሰዳቸውን አረጋግጠዋል።

የባርሴሎና ስፖርት ክለብ በ10 አመታት ውስጥ ለ7ተኛ ጊዜ የላሊጋውን ዋንጫ ማንሳቱን ሲያረጋግጥ በላሊጋው ያገኛቸውን የላሊጋ ዋንጫ በአጠቃላይ 25 ማድረስ ችሏል።

የዘንድሮው የ2017/18 የላሊጋ ክብር ለአሰልጣኙ ኤርኔስቶ ቬልቫርዴ የመጀመሪያቸው ዋንጫ ሲሆን ለአንድሬስ ኢኔስታ እንዲሁም ለሌዬኔል ሜሲ በግል 9ኛ ለሰርጂዋ ቡስኬት እንዲሁም ጀራርድ ፒኬ 7ተኛ የላሊጋ ዋንጫቸው ማንሳታቸውን አረጋግጠዋል።

ባርሴሎና ባልፉት አስር የውድድር ዘመኖች የሊጉን ዋንጫ ብቻ ሳይሆን የተቆጣጠረው የኮፖ ዴላሬ የንጉስን ዋንጫ ስድስቱን በስሙ ማስመዝገብ ችሏል፤ ባጠቃላይ በ10 የውድድር ዘመን 13 ዋንጫዋች የሊጉን እንዲሁም የንጉሱን ዋንጫ ማንሳት ችሏል።

Advertisements