ሜዳው ውስጥ ገብቶ ጨዋታ እንዳይመለከት የተከለከለው ቱርካዊይ ደጋፊ ክሬን በመከራየት ጨዋታውን ተመልክቷል።

Image result for A Turkish football fan banned from his favourite team's stadium has signalled his unwavering passion for Denizlispor by hiring a crane to view a home match.

ፅሁፍ ዝግጅት ፦ መንሀጁል ሀያቲ

የዴኒዚስፐር እግር ኳስ ክለብ ደጋፊ የሆነው ቱርካዊይ ሜዳ ውስጥ ገብቶ እንዳይመለከት በመከልከሉ ምክንያት የሚደግፈው ቡድን 5 ለ 0 ሲያሸንፍ ከሜዳ ውጭ ክሬን ላይ ቁጭ ብሎ መመልከት ችሏል።

በእግር ኳስ የተለያዬ አስቂኝን ነገሮችን መስማማት እና መመልከት የተለመደ ቢሆንም ከወደ ቱርክ የተሰማው አግሞ ይበልጥ ፈገግ ያሰኛል፤ ሁለቱ የቱርክ ክለቦች የሆኑት ክለቦች ዴኒዚስፐር እና ጋዚያንቴፕስፖር ያደረጉትን ጨዋታ ክሬን በመከራየት ተመልክቷል።

የዴኒዚስፐር ደጋፊ የሆነው ሰው የክለቡን ስካርፐ በመልበስ ክለቡን በአገራሚ እይታ ከሜዳ ውጭ ሁኖ መመልከቱ የብዙሀኑን ቀልብ መሳብ የቻለ እና በትልቁ ትኩረትን ማግኘት ችሏል።