ሪያል ማድሪድ ከ ባየር ሙኒክ | የሻምፒዮንስ ሊግ የግማሽ ፍፃሜ የመልስ ጨዋታ ቅድመ ዳሰሳ

ባየር ሙኒኮች ሪያል ማድሪድ በተከታታይ ለሶስተኛ ጊዜ ለፍፃሜ ለመድረስ የሚያደረገውን የተሻለ ተስፋ የመግታት ዕቅድ ይዘው በሻምፒዮንስ ሊጉ የግማሽ ፍፃሜ ጨዋታ ወደስፔን ተጉዘዋል።

ባየር ሙኒክ ባለፈው ሳምንት በመጀመሪያው ጨዋታ በጆሽዋ ኪሚች አማካኝነት ቀዳሚ መሆን ችሎ የነበረ ቢሆንም፣ ነገር ግን በማርሴሎና እና በማርኮ አሰንሲዮ ሁለት ግቦች በገዛ ሜዳው በሪያል ማድሪድ 2ለ1 ከመሸነፍ አልዳነም።

የየፕ ሄንክሱ የጀርመኑ ሻምፒዮን ይህን በበርናባው የሚያደርገውን የምሽት ጨዋታ ቢያንስ በሁለት ግብ ልዩነት ማሸነፍ ይጠበቅበታል።

ይሁን እንጂ በሩብ ፍፃሜው በጁቬንቱስ 3ለ0 ቢመሩም እስከመጨረሻው የጨዋታ ሰዓት ድረስ እጅ ያልሰጡት ማድሪዶች በጉዳት የታመሰውን ባየር ሙኒክን በቀላሉ ይለቁታል ብሎ መጥበቅ አስቸጋሪ ነው።

ጨዋታው መቼ ይደረጋል?

ሪያል ማድሪድ በስፔኗ ዋና ከተማ ማድሪድ፣ በሳንቲያጎ በርናባዩ ባየር ሙኒክን ዛሬ (ማክሰኞ) ምሽት 3፡45 ላይ የሚገጥም ይሆናል።

ጨዋታው በየትኛው ቴሌቭዥን ጣቢያ የቀጥታ ሽፋን ያገኛል?

ከሰሃራ በታች በአፍሪካ ሱፐርስፖርት 3፣ በሰሜን አፍሪካ እና በመካከለኛው ምስራቅ በቤንስፖርት 11 እንዲሁም በዩናይትድ ኪንግደም ቢቲ ስፖርት 3 የቴሌቪዥን ቻናሎች በቀጥታ ይተላለፋል።

ቡድኖቹን የተመለከቱ ምን አይነት ዜናዎች አሉ?

ኢስኮ (በትከሻ ጉዳት) እና ዳኒ ካርቫኻል (በታፋ ጉዳት) በሪያል ማድሪድ በኩል በምሽቱ ጨዋታ ላይ የማይሰለፉ ተጫዋቾች ሲሆኑ፣ በባየር ሙኒክ በኩል ደግሞ በጣም የከፋ የሚባል የጉዳት ችግሮች አሉ።

ጀሮም ቦአቲንግ እስከውድድር ዘመኑ መጨረሻ ድረስ በመጀመሪያው ጨዋታ ላይ በገጠመው የታፋ ጉዳት ከሜዳ ሲርቅ፣ ዴቪድ አላባ ግን በመጀመሪያው ጨዋታ ገጥሞት ከነበረው ጉዳት ሊመለስ ይችላል።

እንዲሁ ከሪያል ጋር በተደረገው ተመሳሳይ ጨዋታ የጡንቻ መናጋት የገጠመው ዣቪ ማርቲኔዝ በዚህ ጨዋታ ላይ ላይሰለፍ የሚችል ሌላኛው ተጫዋች ሲሆን፣ በዚያው ጨዋታ ላይ ሌላው የጉዳት ሰለባ የነበረው አሪያን ሮበን ግን በዚህ ጨዋታ ላይ አለመሰለፉ እርግጥ የሆነ ተጫዋች ነው።

ምን አይነት ግምታዊ አሰላለፎች ይጠበቃሉ?

ሪያል ማድሪድ (4-3-3): ናቫስ፣ ናቾ፣ ቫራን፣ ራሞስ፣ ማርሴሎ፣ ክሩዝ፣ ሞድሪች፣ ካስሚሮ፣ ቫስኬዝ፣ ሮናልዶ፣ ቤንዜማ

ባየር ሙኒክ (4-3-3): ኡልሪች፣ ኪሚች፣ ሱሌ፣ ኹሜልስ፣ ራፊኒሃ፣ ቶሊሶ፣ ቲያጎ፣ ሙለር፣ ሮድሪጌዝ፣ ሪቤሪ፣ ሊቫንዶውስኪ

Advertisements