አርሰናል የሮብ ሆልዲንግን ኮንትራት አደሰ

የ22 ዓመቱ የአርሰናል ተከላካይ ሮብ ሆልዲንግ በክለቡ ለተጨማሪ ጊዜያት የሚያቆየውን የ”ረጅም ጊዜ” የኮንትራት ስምምነት ፈርሟል።

መድፈኞቹ በይፋዊ ድረገፃቸው ላይ ባወጡት መግለጫ “አዲስ ኮንትራቱን አስመልክተን ሮብን እንኳን ደስ አለህ ለማለት እንወዳለን። በቀጣዮቹ ዓመታት ለክለቡ የሚሰጠውን አስተዋፅኦ ዘላቂ እንደሚያደረግም እናስባለን።” ሲሉ ገልፀዋል።

ሆልዲን በዚህ የውድድር ዘመን በሁሉም ውድድሮች ላይ በ24 የክለቡ ጨዋታዎች ላይ ተሰልፎ መጫወት ችሏል።

የእንግሊዝ ከ21 ዓመት በታች ቡድን የመሐል ተከላካይ የሆነው ሆንዲንግ ከቦልተን ወደኤመራትስ ስታዲየም የተዛወረው በ2016 የነበረ ሲሆን፣ ክለቡን በተቀላቀለበት የመጀመሪያ የውድድር ዘመን ከመድፈኞቹ ጋር የኤፍኤ ዋንጫን ማንሳት ችሏል።

ሆልዲንግ በክለቡ ለምን ያህል ጊዜ እንደሚቆይ ግን ክለቡ በመግለጫው ያለው ነገር የለም።

Advertisements