የኬንያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ለብሔራዊ ቡድኑ አዲስ አሰልጣኝ መቅጠሩ አሳወቀ

ፖል ፑት ከለቀቁ በኋላ ተተኪ አሰልጣኝ ሲያፈላልጉ የቆዩት ሀራምቤ ስታርሶቹ በመጨረሻም አዲስ አሰልጣኝ መቅጠራቸውን አሳውቀዋል።

የ 45 አመቱ ፈረንሳዊው ሰባስቲያን ሚኜ ፖል ፖትን ተክተው የሀራምቤ ስታርሶቹ አሰልጣኝ ሆነው በይፋ ተሹሞዋል።

የቀድሞ የኮንጎ አሰልጣኝ የነበሩት ሚኜ ለሶስት አመት ለመቆየት ኮንትራታቸውን የፈረሙ ሲሆን በቆይታቸውም ቡድኑን ለአፍሪካ ዋንጫ ለማሳለፍ ሀላፊነትን ተረክበዋል።

“ለአዲሱ ፈተና በአዲስ ሀገር እዚህ በመገኘቴ በጣም ደስተኛ ነኝ።ስራዬንም ለመጀመር ተዘጋጅቻለው።” ሲሉ ተናግረዋል።

ኬኒያ ኢትዮጵያ በምትገኝበት ምድብ ከጋና እና ሴራሊዬን ጋር በመደልደል ለ 2019 የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ እያደረገች እንዳለች ይታወቃል።