የፈርዲናንድ የቡጢ ተፋላሚነት ህይወት ያለፍልሚያ ተጠናቀቀ

የቀድሞው የማንችስተር ዩናይትድ እና የእንግሊዝ ብሄራዊ ቡድን ተከላካይ ሪዮ ፈርዲናንድ አንድም የቡጢ ፍልሚያ ሳያደርግ የቦክሰኝነት ህይወቱ መጠናቀቁን ገልፅዋል።

የ39 ዓመቱ ፈርዲናንድ ከዚህ ቀደም የቀድሞው በመካከለኛ ክብደት የዓለም ሻምፒዮንና የታላቋ ብሪቴን የቦክስ ቡድን አሰልጣኝ በሆነው ሪቼ ዉዳል ምክር የከባድ ሚዛን ዲቪዥን የቡጢ ፍልሚያን ለመቀላቀል ውሳኔ ላይ ደርሶ ነበር።

ይሁን እንጂ በግል ይፋዊ የፌስቡክ ገፁ ላይ ባሰፈረው መግለጫ የብሪቲሽ የቦክስ ቁጥጥር ቦርድ ለቡጢ ተፋላሚነት የሚያስፈልገውን ፈቃድ ለማግኘት ያቀረበውን ማመልከቻ ሳይቀበለው መቅረቱን ፈርዲናንድ ገልፅዋል።

“ስኬታማ የፕሮፌሽናል የቡጢ ተፋላሚነት ዕቅድ እንዳለኝ ይፋ ካደረግኩበት ጊዜ አንስቶ በሳምንት ለአራት እና አምስት ጊዜ ልምምድ ስሰራ ቆይቻለሁ። ከተለማማጅ ወደተፋላሚ ቡጢኛ ሳልሸጋገር የቡጢ ጓንቴ በመስቀሌ ከፍተኛ ሃዘን ተሰምቶኛል።” ሲል ፈርዲናንድ በመግለጫው አስነብቧል።

ፈርዲናንድ አክሎም “የቡጢ ፍልሚያ በአካል ብቃት በኩል ጥንካሬን የሚሻ አደገኛ ስፖርት ነው። ሁልጊዜም ከፍ ያለ አክብሮቴን ስቸረው ቆይቻለሁ። በንቀት ምን ያህል አስቸጋሪ መሆኑንም ፈፅሞ ዘንግቼ አያውቅም።

“አንዳች ግብ ይዞ እዚያ ላይ መድረስ ምንም ማለት እንዳልሆነ ለሰዎች ማሳየት እሻለሁ። ሁሉንም ነገር በአዕምሮ ስኬትን አንግቦ መጀመር እና ለዚያ ደግሞ ሁሉን ነገር መስጠት አስፈላጊ ነው። ነገር ግን አንዳንድ ጊዜ ነገሮች ከእንተ በተቃራኒ ይሆናሉ።” በማለት ገልፅዋል።

ነገር ግን ፈርዲናንድም ሆነ የብሪቲሽ የቦክስ ቁጥጥር ቦርድ የቀድሞው እግርኳስ ተጫዋች ለመን ፈቃድ ሳይሰጠው እንደቀረ ያሉት ነገር የለም።

Advertisements