የሻምፒዬንስ ሊጉ የፍፃሜ ጨዋታ የእኔ እና የሮናልዶ ፍጥጫ ብቻ አይደለም – ሙሀመድ ሳላህ

Image result for salah and ronaldo

ፅሁፍ ዝግጅት ፦ መንሀጁል ሀያቲ

የ25 አመቱ ግብፃዊ ሙሀመድ ሳላህ የቻምፒዬንስ ሊጉ የፍፃሜ ጨዋታ የግለሰቦች ሳይሆን አጠቃላይ የቡድን ፍልሚ ነው እኔም ቅድሚያ የሚያሳስበኝ የቡድኔ ስኬት ነው ሲል ገለፅ።

የእንግሊዙ ክለብ ሊቨርፑል ከ2007 በሆላ ለሻምፒዬንስ ሊግ ፍፃሜ መድረስ ችሏል በዚህም ጨዋታ ላይ የቀዬቹ ኮከብ የሆነው ሙሀመድ ሳላይ ይህ የፍፃሜ ጨዋታ የማድሪዱ ኮከብ የሮናልዶ እና የእኔ ፍጥጫ አይደለም ሲል ተናግሯል።

ሊቨርፑሎች የጣሊያኑን ሮማን 7 ለ 6 በሆነ የአጠቃላይ ውጤት በማሽነፍ ወደ ኬቭ በመጓዝ ከ12 ጊዜ የሻምፒዬንስ ሊግ ባለክብር ከሆነው የስፔኑ ሀያል ክለብ ሪያል ማድሪድ ጋር የፍፃሜ ጨዋታቸውን የሚያደርጉ ይሆናል።

የፍፃሜው ጨዋታ የሚደረገው እንደ ፈረንጆቹ አቆጣጠር ሜይ 26 / 2018 ዬክሬን ላይ በኬቭ ይሆናል፤ ይህንንም ዋንጫ ሊቨርፑል ካሸነፈ በታሪኩ ለ ስድስተኛ ጊዜ ይሆናል ማድሪድ ካሸነፈ ደግሞ ለ13ተኛ ጊዜ።

Advertisements