የአርሴናሉ አሰልጣኝ አርሴን ቬንገር የደረሰባቸው ሽንፈት ከባድ እንደሆነ ተናገሩ

Image result for wenger

ፅሁፍ ዝግጅት ፦ መንሀጁል ሀያቲ

ላለፉት 22 አመታት በአርሴናል ቤት በአሰልጣኝነት ግልጋሎታቸውን ሲሰጡ የቆዬት አርሴን ቬንገር የአርሴናል ቆይታቸውን ያለ ምንም አውሮፓ ዋንጫ ለመቋጨት ተገደዋል።

አርሴናል በአትሌቲኮ ማድሪድ በደረሰባቸው የ 2 ለ1 ሽንፈት ምክንያት ከአውሮፓ ሊግ ዋንጫ ውጭ መሆናቸውን ተከትሎ ፈረንሳያዊዬ የአርሴናሉ አለቃ አርሴን ቬንገር የደረሰባቸው ሽንፈት ከባድ እንደሆነ ገልፃዋል።

ቬንገር ከምንጊዜውም በላይ እንደተናደዱ እና በሁለቱም ዙር ወርቃማ እድሎችን አለመጠቀማቸው እና በመጀመሪያው ዙር በነበራቸው የተጨዋች ብልጫ አለመጠቀማቸውን እንደ ምክንያትም አቅርበዋል።

አርሴናሎች ትላንት በደርሶ መልስ በአትሌትኮ ማድሪድ በአጠቃላይ 2 ለ 1 በደረሰባቸው ሽንፈት ምክንያት እና በሊጉ በስድተኛ ደረጃ ላይ በመገኘታቸው በቀጣይ አመትም በአውሮፓ ሊጉ ለመቆየት ተገደዋል።

Advertisements