ቼልሲ ከ ሊቨርፑል | የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ቅድመ ዳሰሳ

ሊቨርፑል ለሻምፒዮንስ ሊጉ ፍፃሜ መድረሱን በማረጋገጥ በከፍተኛ ስሜት ውስጥ ሆኖ ይህን ጨዋታ ያደርጋል። ነገር ግን ቼልሲም በቀሩት ሶስት ተጨማሪ ጨዋታዎች የሶስተኝነት ደረጃን ለማግኘት የሚፋለም ይሆናል።

የአንቶኒዮ ኮንቴው በድን ከአንድ እስከአራት ባለው ደረጃ ውስጥ ገብቶ ለማጠናቀቅ ሲልም ጣሊያናዊው አሰልጣኝ እንዳሉት የዛሬው ጨዋታ “ተስፋ”ን ሊሰጣቸው የሚችል ጥሩ ዕድል ሊሆን ይችላል። ለዚህም በተከታታይ ያገኟቸውን ድሎች ለማስቀጠል እንደሚተጉ ሲጠበቅ። በአንፃሩ የሊቨርፑል ያለፉት ሳምንታት ሁለት የፕሪሚየር ሊጉ ጨዋታዎች በአቻ ውጤት የተጠናቀቁ ነበሩ።

ጨዋታው መቼ ይደረጋል?

ቀን፡ እሁድ
ሰዓት፡ አመሻሽ 12፡30
ሜዳ፡ ስታምፎርድ ብሪጅ

ያለፈው ጊዜ ጨዋታ ውጤታቸው ምን ይመስላል?

ቼልሲ 1 ሊቨርፑል 2

ጨዋታውን ማን ይዳኘዋል?

አንቶኒ ቴለር

ዳኛው በዚህ የውድድር ዘመን፡ አጫወቱ25፣ ቢጫ85 ቀይ1፣ 3.44 ካርድ/በጨዋታ

ምን አይነት ግምታዊ አሰላለፎች ይጠበቃሉ?

ቼልሲ

ተቀያሪዎች፡ ካባሌሮ፣ ኤድዋርዶ፣ ኤመርሰን፣ ክርስቲያንሰን፣ ድሪንክዋተር፣ ባካዮኮ፣ ፔድሮ፣ ዛፓኮስታ፣ ባርክሌይ፣ ስተርሊንግ፣ ሁድሰን-ኦዲዮ፣ ሞራታ

መሰለፋቸው የሚያጠራጥሩ፡ ባርክሌይ (በሙሉ ብቃት ላይ አለመገኘት)፣ ድሪንክ ዋተር (በብሽሽት ጉዳት)

ጉዳት ላይ የሚገኙ፡ ዴቪድ ልዊዝ (የጉልበት)፣ አምፓዱ (የቁርጭምጭሚት)

በቅጣት ላይ የሚገኙ፡ የሉም

የተመለከቷቸው ካርዶች፡ ቢጫ38፣ ቀይ4

ወቅታዊ ውጤቶች፡ ድል፣ ሽን፣ አቻ፣ ድል፣ ድል፣ ድል

ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ፡ ሃዛርድ 12


ሊቨርፑል

ተቀያሪዎች፡ ሚኞሌ፣ ማስተርሰን፣ ሞሬኖ፣ ሎቭረን፣ ሶላንኬ፣ ማኔ፣ ጎሜዝ፣ ዋርድ፣ ጆንስ፣ ዉድበርን፣ ሚልነር

መሰፋቸው አጠራጣሪ የሆኑ፡ ጎሜዝ (በቁርጭምጭሚት ጉዳት)

በጉዳት ላይ የሚገኙ፡ ቻን (የጀርባ)፣ ላላና (የቋንጃ) ፣ ማቲፕ (የታፋ)፣ ኦክስሌድ-ቻምበርሌን (የጉልበት)

በቅጣት ላይ የሚገኙ፡ የሉም

የተመለከቷቸው ካርዶች፡ ቢጫ 42፣ ቀይ 1

ወቅታዊ ውጤቶች፡ ድል፣ ድል፣ አቻ፣ ድል፣ አቻ፣ አቻ

ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ፡ ሳላህ 31

Advertisements