“የላሊጋ ዋንጫ የቻምፕየንስ ሊግ ዋንጫን ከማሸነፍ በላይ ከባድ ነው” – ዚዳን 

የማድሪዱ አሰልጣኝ ዜነዲን ዚዳን የላሊጋ ዋንጫን አስጠብቆ በድጋሚ ማሸነፍ የቻምፕየንስ ሊጉ ዋንጫን ከማሸነፍ በላይ ከባድ መሆኑን ተናግሯል።

<!–more–>

ሪያል ማድሪድ ዘንድሮ በላሊጋ እና በቻምፕየንስ ሊጉ እያሳየ የሚገኘው አቋሙ የተገላቢጦሽ ሆኗል።

በላሊጋው በጊዜ ከፉክክሩ ውጪ በመሆን ዋንጫውን ለባላንጣው ባርሴሎና አሳልፎ የሰጠ ሲሆን በቻምፕየንስ ሊጉ ደግሞ ለሶስተኛ ተከታታይ ጊዜ ለፍፃሜ መድረስ ችሏል።

በፍፃሜውም ከሊቨርፑል ጋር የሚፋጠጥ ሲሆን አሸናፊ የሚሆን ከሆነ ዜነዲን ዚዳን ለሶስት ተከታታይ አመት አሸናፊ በመሆን አዲስ ታሪክ መስራት ይችላል።

ፈረንሳዊው ዚዳን በላሊጋው እና በቻምፕየንስ ሊጉ ስላለው ፉክክር ሲናገር 38 ጨዋታዎች ያሉት የላሊጋ ጨዋታዎች ማሸነፍ የቻምፕየንስ ሊጉን ከማሸነፍ በላይ ከባድ መሆኑን ተናግሯል።

“ሁልጊዜ እንደምለው የላሊጋው ዋንጫ ማንሳት በጣም ከባድ ነው።” ሲል የሁለቱን ውድድሮች ልዩነት ያስረዳል።

ማድሪድ እና ባርሴሎና ዛሬ ምሽት ላይ በላሊጋው የሚጫወቱ ሲሆን ባለሜዳዎቹ ሳይሸነፉ የሊጉን ውድድር ለማጠናቀቅ ማድሪዶች ደግሞ የባላንጣቸው ሪከርድ ለመስበር የሚያደርጉት ጨዋታ ይሆናል።

Advertisements