ቬንገር፡ አርሰናል በሚቀጥለው የውድድር ዘመንም በአዲስ አሰልጣኝ ተፎካካሪ መሆን ይችላል

አርሰን ቬንገር የአርሰናል አሰልጠኝነት ሚናን የሚረከባቸው ማንም ሰው ቢሆን “ልዩ” የሆነ የተጫዋች ስብስብ ስላላቸው በ2018-19 የውድድር ዘመን ለፕሪሚየር ሊጉ ዋንጫ መፎካከር እንደሚችል ያምናሉ።

የቬንገር ለ22 ዓመታት በሜዳቸው ያደረጉት የአሰልጣኝነት ዘመን አርሰናል በኢሚራትስ ስታዲየም በርንሌይን 5ለ0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ በቻለበት ጨዋታ ተደምድሟል።

አርሰናል ሁለት ጨዋታዎች ቀርተውት ከውድድር ዘመኑ ሻምፒዮን ማንችስተር ሲቲ በ34 ነጥቦች ዝቅ ብሎ በስድስተኛ ደረጃ ማጠናቀቁን አረጋግጧል።

የሊቨርፑሉ ምክትል አሰልጣኝ ዜሊይኮ ቡቫች፣ ካርሎ አንቸሎቲ፣ ልዊስ ኢነርኬ፣ ዦአኪም ሎው፣ ማሲሚላኖ አሌግሪ፣ ፓትሪክ ቪየራ፣ ሊዮናርዶ ዣርዲም፣ ቴሪ ሆነሪ፣ ሚኬል አርቴታ እና ዡሊያን ናጌልስማን አርሰናልን በአሰልጣኝነት ይረከባሉ ተብለው ስማቸው ከክለቡ ጋር የተቆራኘ አሰልጠኞ ናቸው።

ማን ሊተካቸው ይችል እንደሆነ የተጠየቁት በክለቡ ለረጅም ጊዜ ያገለገሉት ፈረንሳያዊው ሰው አሰልጣኝ በማፈላለጉ ጉዳይ ሃሳባቸውን ለመግለፅ ፈቃደኛ ሳይሆነ ቀርተው ይልቁንስ ክለቡ በሚቀጥለው የውድድር ዘመን ደረጃውን ወደላይ ከፍ ማድረግ የሚችል አቅም እንዳለው መናገርን መርጠዋል።

“ስለሚቀጥለው አሰልጣኝ በአደባባይ አለመናገሬ ጥሩ ይመስለኛል። ምክኒያቱም በታሪኩ ላይ ተሳታፊ አይደለሁም።” ሲሉ የ68 ዓመቱ ቬንገር ከጋዜጣዊው መግለጫው በኋላ የሻምፓኝ ስጦታ ላባረከቱላቸው ጋዜጠኞች ተናግረዋል።

“ይህን ወይም ያንን ምረጥ ብዬ ክለቡ ላይ ጫና ማሳዳር እና ወደዚህ የሚማጣውን ሰው ከወዲሁ አቅመቢስ ላደርገው አልፈልግም። ይህ የእኔ ውሳኔ አይደለም። እኔን ከዚያ ጋር ምንም የሚያገናኘኝ ነገር የለም።

“የማወርሰው ቡድን ሰዎች ከሚያስቡትም በላይ የላቀ ቡድን ነው። በቡድኑ ውስጥ ትልቅ እንድነት ያለ መሆኑን መግለፅ ይኖርብኛል። በጥሩ ሁኔታም በቀጣዩ የውድድር ዘመን የሚፎካከር ይሆናል።”

ቬንገር አርሰናልን ከተሰናበቱ በኋላ በደስታ ስሜት ውስጥ ሆነው በሚቀጥለው የውድድር ዘመን ወደስታዲየሙ እንደሚመለሱ በቀልድ መልክ ተናግረዋል።

“በሰሜናዊው ማቀመጫ በኩል ብቀመጥ እወዳለሁ።” ሲሉ ቬንገር ተናግረው “ይህ ግን የምስራው በሌላ ቦታ መስራት ወይም በአለመስራቴ ላይ የሚመሰረት ይሆናል። የምስራው ምን ቢሆን ግን አርሰናል በሚጫወትበት ቀን ነፃ እሆናለሁ? ትኬት ከሰጣችሁኝ በሰሜናዊው መቀመጫ በኩል ብቀመጥ ደስተኛ ነኝ። አንድ ቦታ ካላችሁም ድንቅ ነገር ይሆናል።

“የዚህ [ደጋፊ የመሆን]መልካም የሆነው ነገር በሰሜናዊው መቀመጫ በኩል ሆኜ በቀጣዩ አሰልጣኝ ላይ መጮኽ መቻሌ ነው።” በማለት ቬንገር ተናግረዋል።

ለሶስት ጊዜያት ያህል የፕሪሚየር ሊግ ሻምፒዮን መሆን የቻሉት አሰልጣኝ ከቀልድ ወደቁም ነገር ተሻግረው ይበልጥ ስሜትን የሚነካ ንግግርም አድርገዋል።

“አንዳንድ ጊዜ ሰዎችን ለማስደሰት ስትል ወደሌላ ቦታ መሄድ ይኖርብሃል።

“እኔም ሰዎች እንዲደሰቱ ፍልጌ ነበር። ምክኒያቱም እኔ እግርኳስ እንዴት መጫወት እንዳለበት የምረዳበት አንዳች የሆነ የራሴ ሃሳብ አለኝ። የእኔ ምኞት ሁልጊዜም በዚህ መንገድ ማሸነፍ ነው። አንተ ትልቅ ክለብ ስትሆን ደግሞ ወደዚያ ክለብ ለሚመጡና ልዩ ተመክሮ ላላቸው ደጋፊዎች የዚያ ኃላፊነት ይኖርብሃል።

“የእኔ ዓላማም ያ ነበር። ሰዎችን ማስደሰት ስልም ያን ማለቴ ነው።”

Advertisements