አንድሬስ ኢኔሽታ የከፍተኛ ክብር ሽልማት ሊበረከትለት ነው

Image result for andres iniesta

ፅሁፍ ዝግጅት ፦ መንሀጁል ሀያቲ

ስፔናዊዬ አንድሬስ ኢኔሽታ በስፔን ስፖርት ከፍተኛ የክብር ሽልማት ሊበረከተለት እንደሆነ ተገለፀ።

የባርሴሎናው የመሀል ሜዳ ሞተር ስፔናዊዬ አንድሬስ ኤኒሽታ በያዝነው ክረምት ለ22 አመታት ሲያገለግል የቆየበትን ክለቡን ባርሴሎናን እንደሚለቅ ካሳወቀ በሆላ ይህ ሽልማት ለኢኔሽታ ሊበረከት እንደሆነ ተገልፆል።

የሽልማቱ አላማ በስፖርቱ ላበረከተው ከፍተኛ ግልጋሎት ክብር ለመስጠት ሲሆን ከዚህ በፊት ይህ ሽልማት የቡድን አጋሩ ለነበሩት ለስፔናዊዬቹ ኢከር ካሲያስ እንዲሁም ዣቪ ኸርናንዴዝ ተበርክቶላቸዋል።

ኢኔሽታ በባርሴሎና ቤት በቆየባቸው 22 አመታት በጣም አስገራሚ የሆነ አቋምን ማሳየት የቻለ ሲሆን በአጠቃላይ 32 ዋንጫዋችን ማንሳት ችሏል።

አንድሬስ ኢኔሽታ ክለቡን እንደሚለቅ በተናገረበት ወቅት ላይ በእንባ ታጅቦ ነበር በስአቱ ከሌዬኔል ሜሲ እና ሊውስ ስዋሬዝ ውጭ ሁሉም የቡድኑ አባላት መገኘት ችለው ነበር።

 

Advertisements