የአውሮፖ እግር ኳስ ማህበር የሻምፒዬንስ ሊጉን የፍፃሜ ጨዋታ የሚዳኙትን ዳኛ አሳወቀ።

 

ፅሁፍ ዝግጅት ፦ መንሀጁል ሀያቲ

የአውሮፖ እግር ኳስ ማህበር የሻምፒዬንስ ሊጉን የፍፃሜ ጨዋታ የሚዳኙት ዳኛ ሰርቢያዊዬ ሚሎራድ ማዚች እንደሆኑ ይፋ አደርጓል።

የ2017/18 የሻምፒዬንስ ሊግ የመጨረሻ ጨዋታ በዬክሬኗ ከተማ ኬቭ ላይ በሪያል ማድሪድ እና በእንግሊዙ ክለብ ሊቨርፑ መካከል እንደሚደረግ የሚታወቅ ሲሆን የአውሮፓ እግር ኳስ ማህበርም የመጨረሻውን ፍልሚያ በብቃት ይዳኙልኛል ያላቸውን ስርቢያዊዬን ሚሎራድ ማዚች መርጧል።

የ45 አመቱ ስርቢያዊይ ዳኛ በአለም አቀፍ ዳኝነት እንደ ፈረንጆቹ አቆጣጠር ከ2009 አመተ ምህረት ጀምሮ የዳኝነት ግልጋሎት እየሰጡ የሚገኙ ሲሆን አለም በጉጉት የሚጠብቀውን የሁለቱን ሀያላን ክለብ ፍጥጫ የሚዳኙ ይሆናል።

ማዚች በያዝነው የውድድር ዘመን በሻምፒዬንስ ሊግ 4 ጨዋታዋችን እንዲሁም በአውሮፓ ሊግ 2 ጨዋታዋችን ማጫወት የቻሉ ሲሆን ፤ በሚሎቫን ሪሲቲች እና ዲሊቦር ጁርድጆቪች በመስመር ዳኝነት እንዲሁም ኒናንድ ጆኪጅ እና ዳኔሎ ጉርጂክ በጎል በኩል በአራተኛ ዳኝነት ደግሞ ክሌመንት ትሩፒን የሚታገዙ ይሆናል።

በአትሌቲኮ ማድሪድ እንዲሁም በማርሴ መካከል የሚደርገውን የአውሮፓ ሊግ የፍፃሜ ጨዋታ ደግሞ ኔዘርላንዳዊዬ ጆርን ኩፐርስ የሚዳኙት ሲሆን ጨዋታው የሚካሄደው በሊዬን ይሆናል።

 

Advertisements