” የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ዋንጫን ማንሳት ከባድ ነው” -ፔፕ ጋርዲዬላ

Image result for pep guardiola premier league champions

ፅሁፍ ዝግጅት ፦ መንሀጁል ሀያቲ

የሲቲው አለቃ ፔፕ ጋርዲዬላ የሊጉን ዋንጫ በእንግሊዝ ማንሳት በስፔን እና በጀርመን የበለጠ በጣም ከባድ ነው ሲል ተናግሯል።

ማንችስተር ሲቲ የ2017/18 የሊግ ዋንጫ ኢትሀድ ስታዲዬም ከሀድርስፊል ጋር 0 ለ 0 አቻ በወጡበት ጨዋታ ማታ ላይ ማንሳት ችለዋል፤ ይህም 2016 ላይ ክለቡን ለተቀላቀለው ለአዲሱ የሲቲ አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዬላ የመጀመሪያ የሊግ ዋንጫ ማንሳት ችሏል።

ፔፕ ጋርዲዬላ ከዚህ በፊት በአስልጣኝነት በሰራባቸው በባርሴሎና እና በባየርሙኒክ በእያንዳንዳቸው ሶስት ጊዜ የሊጉን ዋንጫ ማንሳት የቻለ ሲሆን ከእነዚህ በበለጠ በእንግሊዝ ዋንጫ ማንሳት ከባድ እንደሆነ ሀሳቡን ሰጥቷል። ” እዚህ በጣም ከባድ ነው ,

በእንግሊዝ ልዬ እና ከባድ ነው ምክንያቱም በተፎካካሪዋቹ እና በጥራቱ ፤ በሰራነው ነገር እና በሰራንበት መንገድ ደስተኛች ነን” “የውድድር አመቱ ሲጀመር ምን እንደሚፈጠር አታውቅም ቡድኑን ማዘጋጀት እና ዋንጫው ደግሞ ውጤቱ ነው።

” በቅርብ የውድድር ዘመን ሻምፒዬን የነበሩ ቡድኖቹ በያዝነው የውድድር ዘመን ለሻምፒዬንስ ሊግ ተሳትፎ ማለፍ ሲሳናቸው አይተናል በሊጉ በድጋሚ ዋንጫ ማንሳት ከባድ እንደሆነ አይተናል ይህንንም ፈተና መቀበል ግድ ይለናል።” ፔፕ ጋርዲያላ

Advertisements