ሌስተር ሲቲ ከ አርሰናል | የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ቅድመ ዳሰሳ

አርሰን ቬንገር የመድፈኞቹ የአሰልጣኝነት ዘመናቸው ሊገባደድ ሁለት ጨዋታዎች በቀሩት በዚህ ጊዜ ላይ ሆነው አርሰናልን ይዘው ወደሌስተር ሲቲ በማምራት ይበልጥ ነፃ የሆነ የእግርኳስ አጨዋወት ስልትን እንደሚጠቀሙ ይጠበቃል።

ቬንገር በውድድር ዘመኑ መጨረሻ በአርሰናል ከነበራቸው 22 ዓመታት የሚጠጋ የአሰልጣኝ ዘመናቸውን ለማጠናቀቅ በተቃረቡበት ወቅት ላይ ሆነው በኤመራት ስታዲየም ያደረጉትን የመጨረሻ የስንብት ጨዋታቸውን ባለፈው ሳምንት በርንሌይን 5ለ0 መርታት ችለው ነበር።

አርሰናል በዚህ የውድድር ዘመን የዩሮፓ ሊግ ክብርን ሊቀዳጅ ከሚችልበት እድል ውጪ ቢሆንም ነገር ግን ተጫዋቾቹ በቀሯቸው ሁለት የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች የአርሰን ቬንገርን አንገት ቀና የሚያደርግ አጨዋወት ማሳየትና ጥሩ ውጤት ማስመዝገብን በእጅጉ ይፈልጉታል።

ነገር ግን አርሰናል ከእንግሊዝ የበላይ አራት ክለቦች ሁሉ መጥፎ በተባለ ክብረወሰን በ2018 ከሜዳው ውጪ አንድም የሊግ ነጥብ ማግኘት አልቻለም። ነገር ግን የክላውድ ፑዮሉ ቡድን ባለፈው ጨዋታ የደረሰበት ሽንፈት በዚህ ጨዋታ ላይ ጫና ሊያሳድርበትም እንደሚችል ይጠበቃል።

ጨዋታው መቼ ይደረጋል?

ሌስተር ሲቲ አርሰናል የሚያስተናግድበት ይህ ጨዋታ በኪንግ ፓወር ስታዲየም ዛሬ (ረቡዕ) ግንቦት 1፣ 2010 ዓ.ም ምሽት 3፡45 ላይ የሚደረግ ነው።

ቡድኖቹን የተመለከቱ ምን አይነት ዜናዎች አሉ?

አርሰናል

መሱት ኦዚል በገጠመው የጀርባ ጉዳት ቀሪ የውድድር ዘመን ጨዋታዎች እንደሚያመልጡት ቢጠበቅም ነገር ግን ጀርመናዊው ተጫዋች በጀርመን ብሄራዊ ቡድን የዓለም ዋንጫ ጨዋታዎች ዝግጁ ይሆናል።

ሌላው የአርሰናል ተከላካይ ኮቪየልኒ በገጠመው የተረከዝ ጉዳት የቀዶ ጥገና ህክምና ማድረጉን ተከትሎ ቀሪ የውድድር ዘመን ጨዋታዎች ላይ አይሰለፍም።

ሞሐመድ ኤልኒኒ በቁርጭምጭሚት ጉዳት አሁንም ከሜዳ እንደራቀ ሲቆይ፣ ሳንቲ ካዛሮላ ለረጅም ጊዜ ከሜዳ ካራቀው የጀርባ ጉዳት አገግሞ ከዋናው ቡድን ጋር ልምምድ መስራት ቢጀምርም በፍጥነት ወደጨዋታ ይመለሳል ተብሎ ግን አይጠበቅም።

ሌስተር ሲቲ

የክላውድ ፓየሉ ሌስተር በጉዳት እና በቅጠት የታመሰ ቡድን ሆኖ ሲገኝ ዊልፍሬድ ኢንዲዲ፣ ማርክ ኦልብራይተን (በቅጣት)፣ ቤን ቺልዌል፣ ሮበርት ሁዝ እና ዳንኤል አማርቲ በዚህ ጨዋታ ላይ የማይሰለፉ ተጫዋቾች ናቸው።

እንዲሁም አሌክሳንደር ድራጎቪች፣ ዳኒ ስምፕሰን፣ ሺንጂ ካጋዋ እና ካስፐር ሽሜይክልም መሰለፋቸው ሲያጠራጥር፣ ማቲ ጄምስም እስከውድድር ዘመኑ መጨረሻ ድረስ ወደሜዳ የማይመለስ ሌላኛው ተጫዋች ነው።

ምን አይነት ግምታዊ አሰላለፎች ይጠበቃሉ?

ሌስተር ሲቲ (4-2-3-1): ሃማር፣ ቤናሉኔ፣ ሞርጋን፣ ማጓየር፣ ፉክስ፣ ቻውድኸሪ፣ ኢቦራ፣ ማህሬዝ፣ ሲልቫ፣ ዲያባቴ፣ ቫርዲ

አርሰናል (4-3-2-1): ቼክ፣ ቤለሪን፣ ቻምበርስ፣ ማቭሮፓኖስ፣ ሞንሪል፣ ራምሴ፣ ዣካ፣ ዊልሼር፣ ምክሂታሪያን፣ አውባምያንግ፣ ላካዜቴ

Advertisements