አሜሪካ የ2026 ዓለም ዋንጫን ብታዘጋጅ “ፊፋ ከ8 ቢሊየን ፓውንድ በላይ ያተርፋል”

ፊፋ የ2026 የዓለም ዋንጫ ከሞሮኮ ይልቅ በሰሜን አሜሪካ ቢዘጋጅ ከ8 ቢሊዮን ፓውንድ በላይ ለማትረፍ ዕቅድ መያዙን አዘጋጆቹ ገልፀዋል።

አሜሪካ እ.ኤ.አ. በ1994 ካዘጋጀች ወዲህ በአህጉሪቱ ሲዘጋጅ የመጀመሪያ ለሚሆነው ውድድር በጥምረት ለማዘጋጀት የታጩት አሜሪካ፣ ካናዳና ሜክሲኮ 10.3 ቢሊዮን ፓውድን ትርፍ ለማግኘት የትግበራ ዕቅድ የያዙ ሲሆን፣ የአሜሪካ የእግርኳስ ፕሬዝዳንት የሆኑት ካርሎስ ኮርዴሮ “የምንጊዜውም ስኬታማ የዓለም ዋንጫ” እንደሚሆንም ገልፀዋል።

ይሁን እንጂ ውድድሩን ለማዘጋጀት ከሚፎካከሯቸው ሃገራት መካከል አንዷ የሆነችው ሞሮኮ ባለፈው ሳምንት ወሳኝ የሆኑ ድጋፎችን ማግኘት የቻለች ሲሆን፣ በመጋቢት ወር ላይም ለምን ውድድሩን ማዘጋጀት እንደሚገባት በዝርዝር የሚያብራራ 193 ገፅ ሰነድ ለፊፋ አቅርባለች።

የሞሮኮ ዕጩነት ከአፍሪካ እና የመክካከለኛው ምስራቅ የፊፋ አባል ሃገራት ጠንካራ ድጋፍ ያገኛል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን፣ ፈረንሳይም ድጋፍ ልትሰጣት ዕቅድ ይዛለች። ነገር ግን የአሜሪካኑ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ባለፈው ወር “ጠንካራ”ዋ አሜሪካንን ለማይደግፉት ሃገራት ጫን ያለ ማስጠንቀቂያ ሰጥተዋል።

ትራምፕ በንግግራቸው “እኛ ሁልጊዜም ስንደግፋቸው የነበሩ ሃገራት የአሜሪካንን ዕጩነት በመቃረን ተቃውሞ የሚያቀርቡ ከሆነ አሳፋሪ ጉዳይ ይሆናል። እኛን ሳይደግፉስ ለምንድን ነው ለእነዚህ ሃገራት ድጋፍ የምናደርግላቸው (የተባበሩት መንግስታትንም ጨምሮ)።” ሲሉ ገልፀው ነበር።

ኮርዴሮ ማክሰኞ ዕለት እንዳሉት ከሆነም የፊፋ አባል የውድድር አዘጋጁ ማን ይሁን የሚለውን በቀጣዩ ወር ሲመርጡ ፓለቲካን ወደጎን ይላሉ ብለው ተስፋ እንደሚያደረጉ ተናግረዋል።

“የ2026 ዓለም ዋንጫን ማን ያዘጋጃል የሚለው ጥያቄ በአበቢያዊ ምክኒያቶች ላይ በሚመሰረት ፓለቲካ ጋር ተቆራኝቷል።” ሲሉ ኮርዴሮ ተናግረው “እኛም እየጠየቅን ያለነው ለአዘጋጅነቱ ስለምንገባ እንጂ በአሁኑ ጊዜ ባለው ፓለቲካ አንዳኝ ብለን ነው።” በማለት ገልፀዋል።

የውድድሩን አዘጋጅ ለመወሰን የሚደረገው ምርጫ የ2018 ዓለም ዋንጫ ከሚጀመርበት አንድ ቀን ቀድም ብሎ ረቡዕ ሰኔ 6፣ 2010 ዓ.ም የሚደረግ ይሆናል።

Advertisements