ቼልሲ የ2018/19 አዲስ መለያውን በይፋ አስተዋወቀ

ቼልሲ በ2018/19 አዲሱ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የውድድር ዘመን በሜዳው ለብሶት የሚጫወተውን መለያ በይፋ አስተዋውቋል።

በአሜሪካኑ የትጥቅ አምራች ኩባንያ፣ ናይክ የተመረተው አዲሱ የክለቡ መለያ ስሪቱ በአብዛኛው ተለምዷዊውን ሰማያዊ ቀለም ያያዘ ቢሆንም፣ ነገር ግን አልፎ አልፎ መጨረሻ የሌለቸው የተቆራረጡ ወደጎን የተሰማሩ ቀይና ነጭ ቀለም ያላቸው መስመሮች ሰፍረውበት ለጨዋታ የሚለበሰው እጅግ ተመሳሳዩ መለያ በ90 ፐውንድ እንዲሁም መደበኛው በ65 ፓውንድ ለሽያጭ ቀርቧል።

ሰማያዊዎቹ የሻምፒዮንስ ሊግ ተሳትፎን ለማግኘት በእሁዱ የሊጉ የውድድር ዘመን የመጨረሻ ጨዋታቸው ኒውካሰልን በመርታት በአራተኛ ደረጃ ላይ የሚገኙት ሊቨርፑሎች በብራይተን ነጥብ እንዲጥሉላቸው ተስፋ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል።

ይሁን እንጂ በዚህ የውድድር ዘመን በዋንጫ ማጠናቀቅ የሚችሉበትን ዕድል በኤፍኤ ዋንጫው የፍፃሜ ጨዋታ ማንችስተር ዩናይትድን የሚገጥሙ ይሆናል።

ሁሉንም የቼልሲ አዲስ ትጥቆች ከታች ይመልከቱ።

This slideshow requires JavaScript.

Advertisements