የሊግ ዋንጫ ሳያነሱ በጣም ብዙ አመታትን ያስቆጠሩ 7 ትላልቅ የአውሮፓ ክለቦች

Image result for liverpool epl champions

ፅሁፍ ዝግጅት፡ መንሀጁል ሀያቲ

በጣም ለረጅም አመታት የሊጋቸውን ዋንጫ ሳያነሱ ብዙ አመታት ማስቆጠር የቻሉ በአውሮፖ የሚገኙ ትላልቅ የአውሮፖ ክለቦች በአንደኝነት የእንግሊዙ ክለብ ይመራል ። በአውሮፖ ትላልቅ ሊጎች ላይ እንዲሁም ከሊጉ ባለፈ በአውሮፖ በሚደረጉ ውድድሮች ላይ ጥሩ ፉክክርን ማድረግ የቻሉ ነገር ግን የሊጋቸውን ዋንጫ ለረጅም አመት ማንሳት ያቃታቸውን ክለቦች ይዘንላችሁ ቀርበናል።

7, ስፖርቲንግ ሊዝበን( 15 አመት )

የፖርቹጋሉ ስፖርቲንግ ሊዝበን አካዳሚው እንደ ክሪስቲያኖ ሮናልዶ, ሊውስ ፊጎ እና ናኒን የመሰለ ኮከቦችን ማፍራት ቢችልም ላለፉት 15 አመታት የሊጉን ዋንጫ ማንሳት አልቻለም።

6, ሊቨርፑል ( 27 አመት)

ምንም እንኳን ሊቨርፑል የፕሪሚየር ሊጉን ዋንጫ 18 ጊዜ ማሳካት ቢችልም ላለፉት 27 አመታት ግን ይህንን የሊግ ስኬቱን መድገም ከተሳናቸው ትላልቅ ክለቦች ውስጥ አንዱ ነው።

5, ናፖሊ ( 27 አመት )

የጣሊያን ሴሪ ኤን ለ27 አመታት የናፈቁት ናፖሊዋች በያዝነው የውድድር ዘመን ጥሩ መፎካከር ቢችሉም በስተመጨረሻ በደረስባቸው ነጥብ መጣል ለጁቬ አስልፈው ለመስጠት ተገደዋል።

4, አትሌቲኮ ቢልባሆ ( 33 አመት )

የሁለቱ ፈረሶች ግልቢያ በሆነው የላሊጋው ዋንጫ ፉክክር አትሌቲኮ ቢልባሆ የላሊጋውን ዋንጫ በእጃቸው ከፍ አድርገው ካነሱ ድፍን 33 አመትን ለማስቆጠር ተገደዋል።

3, ኤስ ሴንቲ ኢቴን ( 36 አመት )

በፈረንሳይ ሊግ ኤ በታሪክ ስኬታማ ከሚባሉት ክለቦች ውስጥ አንዱ ነበር ሴንት ኢቴን ፤ የፔስጂ እና የሞኖኮን በተለይ የፔስጂ በሀብት መፈርጠም እና ትላልቅ ክለቦችን ወደ ፈረንሳይ በማምጣት የበላይነት መውስዱን ተከትሎ ላለፉት አመታት ድርቅ መቶታል።

2, ቦርሺያ ሞንቼ ግላድባ ( 40 አመት )

በአውሮፖ ክለቦች ውድድር ላይ አሁንም ድረስ ጥሩ እንቅስቃሴን ማድርግ ይችላል ነገር ግን ለ40 አመታት የጀርመን ቡንደስ ሊጋን ማሳካት ሳይችል ቀርቷል።

1, ቶትንሀም ሆትስፐር ( 56 አመት )

የሞሪስዬ ፖቸቲኖው ቶትንሀም ላለፉት 56 አመታት የሊጉን ዋንጫ ሳያነሱ ለማለፍ ግድ ሁኖል ፤ ቶትንሀም እንደ ማንችስተር ዬናይትድ፤ ቼልሲ፤ ማንችስተር ሲቲ የመሳስሉ ቡድኖችን አልፎ የሊጉን ዋንጫ ማንሳት ትልቅ ፈተና እንደሆነበት አሁንም ቀጥሏል።

Advertisements