ዳኒ አልቬዝ በጉዳት ከራሺያው የአለም ዋንጫ ውጪ ሆነ 

ብራዚላዊው የመስመር ተከላካይ ዳኒ አልቬዝ በጉዳት ከራሺያው የአለም ዋንጫ ውጪ መሆኑ ታውቋል።

35ኛ አመቱ ላይ የሚገኘው እና የራሺያው የአለም ዋንጫ የመጨረሻው የነበረው ዳኒ አልቬዝ በጉዳት ከውድድሩ ውጪ ሆኗል።

ማክሰኞ በፈረንሳይ ዋንጫ ላይ ፔዤ ሌስ ሄርቤርስን ሲገጥም የጉልበት ጉዳት ያጋጠመው አልቬዝ ጉዳቱ ቢያንስ አራት ሳምንታትን የሚፈልግ በመሆኑ ከብራዚል የቡድን ስብስብ የመካተት እድል አይኖረውም።

ተጫዋቹ በመጀመሪያ ከጉዳቱ አገግሞ ለአለም ዋንጫው መሰለፍ እንደሚችል ተጠብቆ የነበረ ቢሆንም በተደረገለት ምርመራ የተጠበቀው ሳይሳካ ቀርቷል።

እንደ ብራዚሉ ግሎቦ ስፖርት መረጃ ከሆነ ደግሞ የብራዚል የህክምና ቡድኖች ከፔዤ ዶክተሮች ጋር በመሆን ለአራት ሰአታት በልምምድ ማእከሉ ውስጥ ቆይተዋል።

ባደረጉት ምርመራን ጉዳቱ መጀመሪያ ከጠበቁት በላይ በመሆኑ ወደ ሜዳ ለመመለስ ቢያንስ ሁለት ወራት እንደሚፈልግ አሳውቀዋል።

Advertisements