የአውሮፖ እግር ኳስ ማህበር ጃንሉጂ ቡፎን በእንግሊዛዊዬ ዳኛ ማይክ ኦሊቨር ላይ በተነገረው ትችት ምክንያት ክስ መሰረተ

Image result for buffon

ፅሁፍ ዝግጅት ፦ መንሀጁል ሀያቲ

ጣሊያናዊ አንጋፋው የአሮጊቷ በረኛ የጁቬንቱስን ከሻምፒዬንስ ሊግ ፍፃሜ ውጭ መሆን ተከትሎ ዳኛው ላይ ባቀረበው ትችት ምክንያት በሁለት ክስ ተላልፎበታል።

በሳንቲያጎ በርናቦ በሻምፒዬንስ ሊጉ የግማሽ ፍፃሜ የመልስ ጨዋታ ላይ ዳኛው ማይክ ኦሊቭር ጨዋታዋ ሊጠናቀቅ ስከንዶች ሲቀሩት በሉካስ ቫስኬዝ ላይ በተሰራው ጥፋት ምክንያት ፍፁም ቅጣት ምት ሰጥተው ሮናልዶ ወደ ጎልነት በመቀየር ማድሪድ ወደ ፍፃሜ ማለፉን አረጋገጠ።

የፍፁም ቅጣት ምቱ በሚሰጥበት ስአት ጃንሉጂ ቡፎን ወደ ማይክ ኦሊቨር በመሄድ ዳኛው ላይ በብስጭት ዳኛውን ያልተገባ ትችት ተችተሀል እንዲሁም ዳኛው በቀይ ካርድ ከሜዳ ማሳወጣተቸውን ተከትሎ በዲሲፕሊን ኮሚቴው ክስ ቀርቦበታል።

የአውሮፖ እግር ኳስ ማህበር የዲሲፕሊን ኮሚቴ በቡፎን ላይ በቀረቡት ሁለት ክሶች ከተመለከተ ብሆላ እንደ አውሮፓዊያኑ የቀን አቆጣጠር ሜይ 31/2018 ውሳኔ የሚያስተላልፍ ይሆናል።

Advertisements