ሹመት / አሌክሳንድሮ ኔስታ የጣሊያኑ ፔሩጂያ አሰልጣኝ ሆኖ ተሾመ

የቀድሞ የላዚዮ እና የሚላን ተከላካይ የነበረው አሌክሳንድሮ ኔስታ የጣሊያኑን ፔሩጂያ አሰልጣኝ ተደርጎ ተሹሟል።

በሴሪ ቢ እየተሳረፈ የሚገኘው ፔሩጂያ ስምንተኛ ደረጃ ላይ በመገኘቱ ወደ ሴሪ ኣ ለማለፍ ለጥሎማለፍ ጨዋታ ቢያልፍም የቡድኑን አሰልጣኝ ሮቤርቶ ብሬዳን አሰናብቷል።

በምትካቸውም አሌክሳንድሮ ኔስታን እስከ ሰኔ 30 ድረስ መተካት የቻሉ ሲሆን አዲሱ አሰልጣኝም በፕሌይኦፍ ጨዋታዎች ላይ ቡድኑን ይዞ ይመራል።

ኔስታ በሰሜን አሜሪካ ውድድር 2016 ላይ የሚያሚ አሰልጣኝ ሆኖ የነበረ ሲሆን በጥሎማለፍ ጨዋታ በኒውዮርክ ኮስሞስ ተሸንፎ ከሀላፊነቱ ተነስቷል።

ኔስታ ጣሊያን ካፈራቻቸው ጠንካራ ተከላካዮች መካከል ዋነኛው ሲሆን በላዚዮ፣በሚላን እንዲሁም በጣሊያን ብሔራዊ ቡድን መጫወት እንደቻለ ይታወሳል።

Advertisements