ሮቤርቶ ማንቺኒ የጣሊያን ብሄራዊ ቡድን አሰልጣኝ በመሆን ተሾሙ

Image result for mancini

የቀድሞው የኢንተር ሚላን እንዲሁም የማንችስተር ሲቲ አሰልጣኝ የነበሩት ሮቤርቶ ማንቺኒ እስከ 2020 ድረስ የአዙሪዋችን በአሰልጣኝነት ለመምራት በይፋ ተሹመዋል።

ፅሁፍ ዝግጅት ፦ መንሀጁል ሀያቲ

ሮቤንቶ ማኒቺኒ ሲያሰለጥኑበት ከነበረው ዚነቲፒተርስ በርግ ክለብ ጋር በጋራ ስምምነት ከተለያዬ በሆላ ከሩሲያው የአለም ዋንጫ ውጭ የሆነውን የጣሊያንን ብሄራዊ ቡድን ለማሰልጠን ተስማምተዋል።

የጣሊያን እግር ኳስ ፌዴሬሽን ኮሚሽነር ሮቤርቶ ፋብሪሲኒ የአዲሱን የጣሊያን ብሄራዊ አሰልጣኝ ሮቤርቶ ማንቺን አድርጎ መሾማቸውን አረጋገጠዋል።ጣሊያን በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ከ2018ቱ የአለም ዋንጫ ውድድር መሆኗን ተከትሎ በቀጣይ ሮቤርቶ ማንቺኒ በአውሮፖ ዋንጫ ላይ የሚሳተፈውን የጣሊያን ብሄራዊ ቡድን ወደ ድሮው አስፈሪነቱ ይመልሱታል ተብሎ ይጠበቃል።

ሮቤርቶ ማንችኒ የአሰልጣኝነት ስራቸውን የጀመሩት በ2001 ላይ በጣሊያኑ ክለብ ፊዬረንቲና ሲሆን ክለቡ አስቸጋሪ ስአት ላይ በነበረበት ጊዜ በመጀመሪያ የውድድር ዘመናቸው የጣሊያን ዋንጫን ማንሳታቸው የሚታወስ ሲሆን በኢንተር ሚላን፤ በማንችስተር ሲቲ እንዲሁም በጋላታሳራይ በአስልጣኝነት መስራት ችለዋል፡፡

Advertisements