ሮናልዶ , ስዋሬዝ , ሳላህ እና ሁሉም የፕሪሚየር ሊጉ የወርቅ ጫማ ተሸላሚዋች።

Image result for mohamed salah epl golden boot

ግብፃዊዬ ሞሀመድ ሳላህ የ217/18 የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ኮከብ ጎል አስቆጣሪ በመሆን የውድድር አመቱ የወርቅ ጫማ ተሸላሚ መሆን ችሏል፤ በሊጉ እስከ አሁን የወርቅ ጫማ ያገኙት እነማን ናቸው? ይዘንላችሁ ቀርበናል።

ፅሁፍ ዝግጅት ፦ መንሀጁል ሀያቲ

1992/93 | ቴዲ ሼሪንግሀም ( 22 ጎሎች )

1992/93 ላይ ቴዲ ሼሪንግሀም በኖቲንግሀም ፎረስት ማሊያ ለመጀመሪያ ጊዜ በስካይ ስፖርት የታየችውን ጎል ማስቆጠር ቻለ, የውድድር አመቱን 22 ጎሎች በማስቆጠር የወርቅ ጫማውን መውሰድ ችሏል።

1993/94 | አንዲ ኮል ( 34 ጎሎች ) አንዲ ኮል በኒውካስትል ማሊያ 34 ጎሎችን በማስቆጠር 1993/94 ላይ የውድድር አመቱን ማጠናቀቅ ችሏል።

1994/95 | አለን ሸረር ( 34 ጎሎች )

የፕሪሚየር ሊጉ የምንግዜም ጎል አስቆጣሪ የሆነው አለን ሸረር ከብላክበርን ጋር በመሆን የወርቅ ጫማውን በ34 ጎሎች ማሳካት ችሏል።

1995/96 | አለን ሸረር ( 31 ጎሎች )

በብላክበርን ማሊያ አለን ሺረር በፕሪሚየር ሊጉ በሁለት ተከታታይ የውድድር ዘመን የወርቅ ጫማ መውሰድ የቻለበትን ታሪክ መስራት ቻለ።

1996/97 | አለን ሸረር( 25 ጎሎች )

አለን ሺረር ወደ ኒውካስተል ተጉዞ በፕሪሚየር ሊጉ በተከታታይ ለ3ተኛ አመት የሊጉ ኮከብ ጎል አስቆጣሪ በመሆን ታሪክ መስራት ቻለ።

1997/98 | ክሪስ ሱቶን, ማይክል ኦይን እና ዲዬን ደብሊን ( 18 ጎሎች )

የ1997/98 የውድድር አመት ሶስት አሸናፊዋች በተመሳሳይ ጎል የጨረሱበት የውድድር አመት ነበር።

1998/99 | ማይክል ኦይን, ዋይት ዬርክ እና ጂሚፍሎይድ ( 18 ጎሎች )

የ1998/99 የውድድር አመት ሶስት አሸናፊዋች በተመሳሳይ ጎል የጨረሱበት የውድድር አመት ነበር። 1999/2000 | ኬቨር ፊሊፕስ ( 30 ጎሎች )

በሲዝኑ ከሰንደርላንድ ጋር ጥሩ ጊዜን ማሳለፍ የቻለው ኬቨን ከፕሪሚየር ሊጉ በተጨማሪ የአውሮፓ ኮከብ ጎል አስቆጣሪነትን ክብር ማግኘት ችሏል።

2000/2001 | ጂሚ ፍሎይድ ( 23 ጎሎች )

ጂሚ በቼልሲ ማሊያ 23 ጎሎችን ማስቆጠር የቻለ ሲሆን ክለቡ በሊጉ 6ተኛ ደረጃ ላይ ነበር መጨረስ የቻለው።

2001/2002 | ቴሪ ሄነሪ ( 24 ጎሎች )

ሄነሪ በውድድር አመቱ በአርሰናል ቤት የመጀመሪያ የወርቅ ጫማውን ማሳካት ቻለ።

2002/2003 | ሩድ ቫልኒስተር ሮይ ( 25 ጎሎች )

በውድድር አመቱ ማንችስተር ዬናይትድ የሊጉን ዋንጫውን ሲነሳ ሩድ የወርቅ ጫማውን ማሳካት ችሏል።

2003/2004 | ቴሪ ሄነሪ ( 30 ጎሎች )

በዚህ አመት ሄነሪ የወርቅ ጫማውን ማንሳቱ አያስገርምም ምክንያቱም አርሴናል ዋንጫውን ሲነሳ ምንም አይነት ሽንፈት ሳያስተናግድ ነበር።

2004/2005 | ቴሪ ሄነሪ ( 25 ጎሎች )

ሄነሪ በ 32 ጨዋታዋች 25 ጎሎች ማስቆጠር ሲችል አርሴናል በቼልሲ ተበልጦ 2ተኛ ደረጃን ይዞ ማጠናቀቅ ችሏል።

2005/2006 | ቴሪ ሄነሪ ( 27 ጎሎች )

ፈረንሳያዊዬ ኮከብ ለሶስት ተከታታይ አመት በመሸለም የአለን ሺረርን ክብረ ወሰን መጋራት ሲችል ለአራተኛ ጊዜ በመሸለም ሪከርድ መያዝ ችሏል።

2006/2007 | ዲዲየር ድሮግባ ( 20 ጎሎች )

ድሮግባ የወርቅ ጫማውን በመሸለም የመጀመሪያ አፍሪካዊ ተጨዋች መሆን ችሏል።

2007/2008 | ክሪስቲያኖ ሮናልዶ ( 31 ጎሎች )

ፖርቹጋላዊዬ የአለማችን ኮከብ ሮናልዶ በማንችስተር ማሊያ ማሳካት ችሏል።

2008/09 | ኒኮላስ አኒልካ ( 19 ጎሎች ) አኒልካ

ከአስራ ሁለት አመት የፕሪሚየር ሊግ ቆይታ በሆላ በቼልሲ ማሊያ የመጀመሪያውን ሽልማቱን ማግኘት ችሏል።

2009/2010 | ድሮግባ ( 29 ጎሎች ) ቼልሲ ከዊጋን ጋር በተጨዋቱበት የ 8 ለ 0 ጨዋታ ላይ ድሮግባ ሀትሪክ መስራት በመቻሉ ለሁለተኛ ጊዜ ማሳካት ችሏል።

2010/11 | ካርሎስ ቴቬዝ እና ዲሜትሪ ቤርባቴቭ ( 20 ጎሎች )

በውድድር ዘመኑ ሁለቱ ኮከቦች ካርሎስ ቴቬዝ እና ዲሜትሪ ቤርባቴቭ በጥምረት ማሸነፍ ችለዋል። 2011/12 | ሮቨን ቫንፔርሲ ( 30 ጎሎች )

በውድድር ዘመኑ አርሰናል 3ተኛ ደረጃን ይዞ እንዲያጠናቅቅ ቫንፔርሲ መርዳት ችሏል።

2012/13 | ሮቨን ቫንፔርሲ ( 26 ጎሎች )

ቫንፔርሲ በቀጣዬ አመትም በዬናይትድ ቤት በመዘዋወር የወርቅ ጫማውን ማሳካት ችሏል: ዬናይትድም ዋንጫውን ማንሳት ችሏል።

2013/14 | ሊውስ ስዋሬዝ ( 31 ጎሎች )

ስዋሬዝ ኢቫኖቪችን በመማታቱ ምክንያት የተወስኑ ጨዋታዋች በቅጣት ቢያልፉትም 31 ጎሎችን በማስቆጠር የሊጉ ኮከብ ጎል አስቆጣሪ በመሆን ጨርሷል።

2014/2015 | ሰርጂዋ አጉዌሮ ( 26 ጎሎች )

አጉዌሮ በ 33 ጨዋታዋች 26 ጎሎችን በማስቆጠር የወርቅ ጫማውን መሸለም ችሏል።

2015/16 | ሀሪ ኬን ( 25 ጎሎች ) ሀሪ ኬን በ38 ጨዎታዋች 25 ጎሎችን በማስቆጠር ከአጉዌሮ እና ከጅሚ ቫርዲ በላይ በመሆን ሽልማቱን ማግኘት ችሏል።

2016/17 | ሀሪ ኬን ( 29 ጎሎች )

2016/17 የውድድር አመት ሀሪኬን ከሄነሪ በሆላ ለሁለት ተከታታይ አመታት የወርቅ ጫማ መሸለም የቻለበት አመት መሆን ችሏል።

2017 / 18 | ሙሀመድ ሳላህ ( 32 ጎሎች ) ከጣሊያን ወደ እንግሊዝ በተዘዋወረበት አመት በሊቨርፑል ቤት የማይረሳ ጊዜን ማሳለፍ የቻለው ሙሀመድ ሳላህ በ38 ጨዋታዋች 32 ጎሎችን በማስቆጠር የወርቅ ጫማውን መሸለም የቻለ ሁለተኛው አፍሪካዊይ ተጨዋች መሆን ችሏል።

Advertisements