ባለፉት 48  ስአት ውስጥ ምንም ምን ተፈጠረ?

 

ኢትዬ አዲስ ስፖርት ባለፉት 48  ስአት ውስጥ የተከናወኑ ድርጊቶችን እና ዜናዋችን አጥር ባለ መልኩ ይዘንላችሁ ቀርበናል እንደሚከተለው አቅርበንላቸዋል፡፡

ፅሁፍ ዝግጅት ፦ መንሀጁል ሀያቲ

  • በስፖኒሽ ላሊጋ 37ተኛ ሳምንት ጨዋታ ባርሴሎና በሌቫንቴ ባጋጠመው 5 ለ 4 የሆነ ሽንፈት በላሊጋው ያለመሸነፍ ክብረ ወሰኑ መገታት ችሏል። በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ሊቨርፑል የሻምፒዬንስ ሊግ ተሳትፎውን ማረጋገጥ ሲችል የ2016/2017 የሊጉን ዋንጫ ማንሳት የቻለው ቼልሲ በኒውካስትል ሶስት ለ ዜሮ በመሸነፍ ከአውሮፖ ሻምፒዬንስ ሊግ ውጭ ሁኗል።
  • የአርሰን ቬንገር 828ተኛ የፕሪሚየር ሊግ እና 1235ተኛ በሁሉም ውድድር ላይ የሆነው የመጨረባው የአርሴናል ጨዋታ ከሜዳ ውጭ ሀደርስፊልድን 1 ለ 0 በማሸነፍ ተደምድሟል።
  • በጣሊያን ሴሪያ ጁቬንቱስ ከ ሮማ ጋር ዜሮ ለ ዜሮ በሆነ አቻ ውጤት በመውጣት ለሰባተኛ ጊዜ የስኩዴቶውን ዋንጫ ማንሳቱን አረጋግጧል፤ አሰልጣኙም ማስሚላኖ አሌግሬ በአሮጊቷ ቤት መቆየት እንደሚፈልግ ተናግሯል።
  • ብራዚላዊዬ ኔማር የፈረንሳይ ሊግ አንድ የአመቱ ኮከብ ተጨዋች በመሆን መመረጥ ችሏል፤ ከሊውስ ናዛሪሆ ዶሊማ ሮናልዶ ሽልማቱንም መቀበል ችሏል።
  • ግብፃዊዬ ሙሀመድ ሳላህ በ38 የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዋች 32 ጎሎችን በማስቆጠር የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የ2017/18 የወርቅ ጫማ መሸለም ችሏል። ሊዬኒል ሜሲ በውድድር አመቱ 34 የላሊጋ ጎሎችን በማስቆጠር የስፖኒሽ ላሊጋን የአመቱ ከፍተኛ ጎል አስቆጣሪ በመሆን የወርቅ ጫማ መሸለም ችሏል።
Advertisements