ዮአኪም ሎው ለ ብሔራዊ ቡድን ያልጠሯቸው ሰባቱ ጀርመናዊ ኮከቦች

የጀርመን ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ የ 58 አመቱ ዩአኪም ሎው ለብሔራዊ ቡድኑ 27 ተጫዋቾችን ሲመርጡ ሰባት ኮከቦችን ሳይጠሩ ቀርተዋል።

​የ 2018 የአለም ዋንጫ ሊጀመር ከወር ያነሰ ጊዜ በቀረበት ወቅት ሀገራት ጊዚያዊ ቡድናቸውን እያሳወቁ ይገኛሉ።

የ2014 ሻምፕዮኗ ጀርመንም ቡድኗን ይፋ የደረገች ሲሆን ስም ያላቸው ሰባት ተጫዋቾችን ሳታካትት ቀርታለች።

2014 የፍፃሜ ጨዋታ ላይ የማሸነፊያዋን ጎል ያስቆጠረው ማሪዮ ጎትዘ ከጥሪው ውጪ ከሆኑት ውስጥ ተካቷል።ሌላው የቡድን አጋሩ አንድሬ ሹርለም ጥሪው የዘለለው ሆኗል።

በፕሪምየርሊጉ የሚጫወቱት ኤምሬ ቻን እና የአርሰናሉ ሽኮርዳን ሙስጣፊ የአለም ዋንጫውን በቴሌቭዥን የሚከታተሉ ስመጥር ጀርመናዊያን ናቸው።

ሳንድሮ ቫግነር(ባየርሙኒክ)፣ላርስ ስቲንድል(ቦሩሲያ ሞንችግላድባህ) እና ቤኔዲክት ሀውደስ(ጁቬንቱስ) ጥሪው ያመለጣቸው ሌሎች ኮከብ ተጫዋቾች ናቸው።

ጀርመን በአለም ዋንጫው በምድብ 6 ከ ሜክሲኮ፣ስዊዲን እና ደቡብ ኮሪያ ጋር መደልደሏ ይታወሳል።