ባለፉት 24 ስአት ውስጥ ምንም ምን ተፈጠረ?

 ኢትዬ አዲስ ስፖርት ባለፉት 24 ስአት ውስጥ የተከናወኑ ድርጊቶችን እና ዜናዋችን አጥር ባለ መልኩ ይዘንላችሁ ቀርበናል፡፡
  • ስፔናዊዬ የማንችስተር ሲቲ አስልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ የ2017/18 የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የአመቱ ምርጥ አስልጣኝ በመሆን ተሸለመ።
  • የቀድሞው የአስቶቪላ ተከላካይ የነበረው ጅሌይድ ሳሙኤል ባጋጠመው የመኪና አዳጋ ምክንያት በ37 አመቱ ከዚህ አለም በሞት ተለይቷል።
  • ለ2018ቱ የአለም ዋንጫ የተለያዬ ብሄራዊ ቡድኖች የቡድኖች በአለም ዋንጫው ላይ የሚያሳትፏቸውን ተጨዋቾች ስብስብ በይፋ ያሳወቁ ሲሆን በሳውዝ ጌት የሚመራው የእንግሊዝ ብሄራዊ ቡድን ያለ ጃክ ዊልሸር እንዲሁም ጆ ኸርት ወደ ሩሲያ እንደሚያቀና ይፋ ሁኗል።
  • አርጀንቲናዊዬ የኳስ ጥበበኛ ሊዬኔል ሜሲ የአለም ዋንጫው ከመጀመሩ በፊት ወደ ጣሊያን አምርቶ ነበር ምክንያቱም ደግሞ የአለም ዋንጫ ከመድረሱ በፊት የምግብ ባለሙያ የሆነውን ዶክተር ጁሊያኖ ፖሰርን ለማማከር እንደሆነ ተነግሯል።
  • ቤልጄማዊዬ ኤዲን ሀዛርድ በቼልሲ ቤት ወደፊት ኮንትራቱን እንዲያድስ ጥሩ ተጨዋቾች ወደ ክለቡ እንዲመጡ እንደሚፈልግ ተናግሯል።
  • የማንችስተር ዬናይትዱ እስፔናዊዬ ኢንተርናሽናል አንድሬ ሄሬራ ምንም እንኳን ሙሀመድ ሳላህ ብዙ ነገሮችን ማሳካት ቢችልም የፕሪሚየር ሊጉ ምርጥ ተጨዋች ኤዲን ሀዛርድ ነው ሲል ተድምጧል።
  • ዮሀኪም ሎው በጀርመን ብሄራዊ ቡድን አስልጣኝነት እስከ 2022 ድረስ የሚያቆየውን ኮንትራት ፈርመዋል፤ የጀርመን እግር ኳስ ፌዴሬሽን የብሄራዊ ቡድኑ አስልጣኝ ለተጨማሪ አራት አመታት በአስልጣኝነት የሚያቆያቸውን ተጨማሪ ኮንትራት ማራዘማቸውን ይፋ አድርጓል።

 

 

Advertisements