የሮናልዶ መሸጥ በሪያል ማድሪድ “የተከለከለ” ጉዳይ መሆኑን ሞሪንሆ ተናገሩ

ጆዜ ሞሪንሆ የሻምፒዮንስ ሊጉ የፍፃሜ ተፋላሚ ሪያል ማድሪድ የክርስቲያኖ ሮናልዶን የመሸጫ ዋጋ ለመግለፅ ፈቃደኛ ባለመሆኑ ተጫዋቹ ሪያል ማድሪድን ይለቃል ብለው አያምኑም።

የማንችስተር ዩናይትዱ አሰልጣኝ በሻምፒዮንስ ሊጉ ፍፃሜ ግንቦት 18፣ 2010 ዓ.ም በኪየቩ የፍፃሜ ጨዋታ ከሊቨርፑል ጋር በሚፋለመው ሪያል ማድሪድ ከሮናልዶ ጋር አብረው ሰርተዋል።

ሮናልዶ ለመዛወር የሚችልበት ዕድል ካለ ለዝውውሩ ፈቃደኝነታቸውን ወዳሳዩትና በሞሪንሆ ወደሚሰለጥነው የኦልትራፎርዱ ክለብ ሊመለስ ስለመሆኑ የሚፈገልፁ ተደጋጋሚ የጭምጭምታ ዘገባዎች ሲወጡ ቆይተዋል።

ነገር ግን ሪያል ማድሪድ የተጫዋቹን የዝውውር ዋጋ ለመግለፅ ፈቃደኝነት ያለው አለመምሰሉን ተከትሎ ሞሪንሆ የ33 ዓመቱ ፓርቱጋላዊ ኮከብ ከሳንቲያጎ በርናባው ይለቃል ብለው አይጠብቁም።

“ሪያል ማድሪድ ይሸጠዋል ብዬ አላስብም። ያ የተከለከለ ነገር ነው።” ሲሉ ሞሪንሆ ሪከርድ ለተሰኘው የፓርቱጋል ጋዜጣ ተናግረዋል።

“እነሱ እሱ እንዲሄድ እና ለአንድ ዓመት እሱን በሚያስደስተው አሜሪካ ወይም በሌላ ቦታ እንዲጫወት እስኪፈቅዱለት ድረስም የግድ የሚቆይ ይሆናል። ጉዳዩ የተዘጋ በር ነው።” በማለትም ሞሪንሆ ጨምረው ገልፀዋል።

ሮናልዶ ወደዩናይትድ ሊመለስ ስለሚችልበት ሁኔታ ሞሪንሆ “አይመለኝም። ነገር ግን ሁሉም ሰው እሱ በማንችስተር ለነበረው ታሪክ እና እነሱ ለእሱ ያለቸውን ጥልቅ ስሜት ያውቃል። ክለቡ ሊያስፈርማቸው የሚችልባቸው ሁኔታዎች ካሉ የክለቡን ጥያቄ እምቢ የማይሉ በርካታ ተጫዋቾች በዓለም ላይ አሉ።” በማለት ተናግረዋል።

ሞሪንሆ የፖርቱጋልን ብሄራዊ ቡድን በማሰልጠን ከሮናልዶ ጋር ዳግመኛ ሊገናኙ የሚችሉበት ዕድል እንዳለ ፍንጭ ሰጥተው፣ ነገር ግን እስከአሰልጣኝነት ዘመናቸው መጨረሻ ድረስ ክለብ የማሰልጠን ሚናቸውን መልቀቅ እንደማይፈልጉ ተናግረዋል።

“በአንድ ወቅት ወደዚያ [ወደፓርቱጋል አሰልጣኝነት ሚና] ለማምራት ተቃርቤ ነበር። ነገር ግን ፍሎረንቲኖ ፔሬዝ አለቀቀኝም። ምክኒያቱም እሱ ሪያልን የማሰልጠን ጥልቅ ስሜት ብሄራዊ ቡድንን ከማሰልጠን ጋር አብሮ እንደማይሄድ አስቦ ነበር።” ሲሉ ሞሪንሆ ተናግረዋል።

Advertisements