አጉዌሮ፡ እኔ በማንችስተር ሲቲ መሲ ደግሞ በባርሴሎና እንቆያለን

የማንችስተር ሲቲው አጥቂ ሰርጂዮ አጉዌሮ እሱ በፕሪሚየር ሊጉ ሻምፒዮን ክለብ፣ የባርሴሎና ኮከብ ደግሞ በላ ሊጋው ሻምፒዮን ክለብ እንደሚቆዩ በመግለፅ ከሊዮኔ መሲ ጋር አብሮ መጫወት የሚችልበት ሁኔታ እንደማይኖር ገልፅዋል።

ለሶስተኛ ጊዜ የፕሪሚየር ሊጉን የዋንጫ ክብር የተቀዳጀው የ29 ዓመቱ አርጄንቲናዊው አጥቂ በሚቀጥለው ወር በሩሲያ ለሚደረገው የዓለም ዋንጫ ውድድር ራሱን እያዘጋጀ የሚገኝ ቢሆንም፣ ክለቡን ይለቃል በሚል ስሙ ከሌሎች ክለቦች ዝውውር ጋር ተያይዞ ይገኛል።

የሲቲው አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ አጉዌሮ በክለቡ በሚኖረው የወደፊት ዕጣ ፈንታ ላይ ጥያቄ እየቀረበባቸው እንደሚገኝ ዘገባዎች እያመለከቱ የሚገኝ ሲሆን፣ የቀድሞው የአትሌቲኮ ማድሪድ ተጫዋች መዳረሻ ደግሞ ባርሴሎና ሊሆን እንደሚችልም አመልክተዋል።

ነገር ግን ከአምስት ጊዜው የባሎን ዶር አሸናፊውና ከአርጄንቲናዊው የሃገሩ ልጅ ሊዮኔል መሲ ጋር አብሮ ሊጫወት ስለሚችልበት ሁኔታ ጥያቄ የቀረበለት የ30 ዓመቱ አጥቂ እና እስከ2020 ድረስ የሚዘልቅ የኮንትራት ስምምነት ያለው አጉዌሮ “ያ ከመሆኑ ቢፊት ለእኔም ሆነ ለእሱ ጥያቄው የዕድሜ ሩዳይ ነው። እሱ ጥሩ እየተጫወተ በሚገኝበት ባርሴሎና ይቆያል። እኔ ደግሞ በሲቲ።” በማለት ለቲዋይሲ ተናግሯል።

አጉዌሮ በአጠቃላይ ውድድሮች ላይ ለሲቲ ባደረጋቸው የ2016/18 የውድድር ዘመን ጨዋታዎች 30 ግቦችን ከመረብ ላይ ማሳረፍ የቻለ ሲሆን፣ ለእነዚህ መካከል 21 ግቦችን ያስቆጠረው በፕሪሚየር ሊጉ ላይ ነበር።

Advertisements