ባርሴሎና የ2018/19 የውድድር ዘመን አዲስ መለያውን በይፋ አስተዋወቀ

የላ ሊጋው ሻምፒዮን ባርሴሎና ባልተለመደ ሁኔታ ባርሴሎና ከተማን በሰማይ ላይ እያንዣበበች በዞረች ድሮን ላይ በማድረግ በቁጥር 10 የሆኑ ሰማያዊ እና ቀይ ቁልቁል መስመሮች ያሉትን የሚቀጠለው የውድድር ዘመን መለያውን በይፋ አስተዋውቋል።

ባርሴሎና በአሜሪካው የትጥቅ አምራቹ ናይክ የተመረተውን አዲስ መለያውን ለማስተዋወቅ የቀድሞው የሊቨርፑል ኮከብ ፊሊፔ ኮቲንሆ ተጠቅሞ ተጫዋቹ መለያውን ለብሶ በይፋ በ1992ቱ የኦሎምፒክ ስታዲየም ተገኝቷል።

ናይክ መለያውን አስመልክቶ በድረገፁ በለቀቀው መግለጫ በመለያው ላይ የሰፈሩት አስሩ መስመሮች በከተማዋ ያሉትን አስር ቀጠናዎች እንዲያመላክቱ በማስብ መስራቱን ገልፅዋል።

Advertisements