ቼልሲ ከ ማንችስተር ዩናይትድ | የኤፍኤ ዋንጫ የፍፃሜ ፍልሚያ ቅድመ ዳሰሳ

ቼልሲና ማንችስተር ዩናይትድ በ2018 የውድድር ዘመን ዛሬ [ቅዳሜ] በኤፍኤ ዋንጫ የፍፃሜ ጨዋታ የዋንጫ ክብርን ለመቀዳጀት ይፋለማሉ።

ጨዋታው መቼና የት ይደረጋል?

በቼልሲና በማን ዩናይትድ መካከል የሚደረገው የኤፍኤ ዋንጫ የፍፃሜ ጨዋታ ዛሬ [ቅዳሜ] ምሽት 1፡15 ላይ በለንደኑ ዌምብሌይ ስታዲየም የሚደረግ ነው።

ጫዋታውን ማን ይዳኘዋል?

ይህን ጨዋታ በመኃል ዳኛነት ማይክል ኦሊቨር የሚመሩት ይሆናል።

እሰልጣኞቹ ስለጨዋታው ምን አሉ?

አንቶኒዮ ኮንቴ “ይህ ጨዋታ ለእኛ በጣም ወሳኝ ነው። ምክኒያቱም የውድድር ዘመኑን ያለዋንጫ የምናጠናቅቅበት አስቸጋሪ የውድድር ዘመን ነው።

“ሁልጊዜም የውድድር ዘመኑን በዋንጫ ማጠናቀቅ ለተጫዋቾቹ፣ ለአሰልጣኞቹ፣ ለደጋፊውና ለክለቡ ፋይዳ አለው።

“ዒላማችን ላይ ትኩረት አድርገናል። የነገውን ጨዋታ ለማሸነፍ ሁሉንም ነገር ለማድረግ ጥረት እናደርጋለን።

ጆዜ ሞሪንሆ፡ “እርግጥ ነው ልዩነት ያመጣል። ነገር ግን አንዱ ነገር ለውጥ ማምጣት ነው። እና ደግሞ ሌላኛው በአንድ ጨዋታ ምክኒያት የውድድር ዘመኑን ጥሩ ወይም መጥፎ እንደሆነ
የምንወስድበት ነው።

“የሰራሁትን ስራ ሳጤነው፣ ያደረግኩትን ጥረት ከግምት ውስጥ ሳስገባው ለክለቡ ያደረግናቸውን ነገሮች በሙሉ ሳስበው ለክለቡ ወሳኝ የሆኑት ሰዎች፣ ተጫዋቾቹን በዚህ ውስጥ ማካተቴ ግልፅ ነው።

“በጣም ወሳኝ በሆነ አንድ ጨዋታ ምክኒያት እነሱን አልገምታቸውም። ነገር ግን ተጫዋቾቼ የሰሩትን ነገር አውቃለሁ፣ እኔም ምን እንዳደረግኩ አውቃለሁ። ጥረቱን፣ አዎንታዊን እና አሉታዊ ነገሮችንም አውቃለሁ። ስለዚህ በአንድ ውጤት ምክኒያት በውድድር ዘመኑ ላይ ያለኝን ጥልቅ ትንታኔያዊ ግንዛቤ አለውጥም። ፈፅሞ።”

ክለቦቹ ለፍፃሜ የደረሱባቸው ጨዋታ ውጤቶች ምን ይመስሉ ነበር?

ቼልሲ

ሶስተኛ ዙር – ከኖርዊች ሲቲ (ከሜዳ ውጪ) 0–0

ሶስተኛ ዙር የመልስ ጨዋታ – ከኖርዊች ሲቲ (በሜዛው) 1–1 (5–3 በማለያ ምት)

አራተኛ ዙር – ከኒውካሰል (ከሜዳውጪ) 3–0

አምስተኛ ዙር – ከኸል ሲቲ (በሜዳው) 4–0

ሩብ ፍፃሜ – ከሌስተር (በሜዳው) 2–1

ግማሽ ፍፃሜ – ከሳውዛምፕተን (በዌምብሌይ) 2–0

ማን ዩይትድ

ሶስተኛ ዙር – ከደርቢ ካውንቲ (በሜዳው) 2–0

አራተኛ ዙር – ከዮቬል ታውን (ከሜዳው ውጪ) 4–0

አምስተኛ ዙር – ከኸደርስፊልድ (ከሜዳው ውጪ) 2–0

ሩብ ፍፃሜ– ከብራይተን (በሜዳው) 2–0

ግማሽ ፍፃሜ– ከቶተንሃም (በዌምብሌይ) 2–1

ምን ዓይነት የመጀመሪያ ግምታዊ አሰላለፎች ይጠበቃሉ?

ቼልሲ፡ ኮርቱዋ፣ ሞሰስ፣ አዝፔሉኬታ፣ ካሂል፣ ሩዲገር፣ አሌንሶ፣ ካንቴ፣ ፋብሪጋዝ፣ ዊሊያን፣ ዥሩ፣ ሃዛርድ

የማይሰለፉ፡ ድሪንክዋተር፣ ልዊዝ፣ ኤመርሰንና አምፓዱ

ማንችስተር ዩናይትድ፡ ደ ኽያ፣ ቫሌንሺያ፣ ጆንስ፣ ስሞሊንግ፣ ያንግ፣ ማቲች፣ ሄሬራ፣ ፓግባ፣ ሊንጋርድ፣ ሉካኩ፣ ሳንቼዝ

መሰለፋቸው የሚያጠራጥር፡ ሉካኩ እና ፌላኒ

Advertisements