አርቴታ የመድፈኞቹ አሰልጣኝ ለመሆን ስምምነት ላይ ደረሰ

እንደ ታላላቆቹ የዜና አውታሮች መረጃ ከሆነ አርቴታ አርሴን ዌንገርን ተክቶ የመድፈኞቹ አሰልጣኝ ለመሆን በመርህ ደረጃ ስምምነት ላይ መድረሱን ገልፀዋል።

የቀድሞ የኤቨርተን እና የመድፈኞቹ አማካይ የነበረው ሚኬል አርቴታ 2016 ላይ ከመድፈኞቹ ጋር በጡረታ እስከተለያየበት ድረስ 150 ጨዋታዎችን አድርጓል።

በመቀጠል ወደ ሲቲ በማቅናት የፔፕ ጓርዲዮላ ረዳት በመሆን የፕሪምየርሊጉን ዋንጫ ከተለያዩ ሪከርዶች ጋር በማጣጣም ስኬታማ ቆይታ አድርጓል።

አሰልጣኙ ብዙ የማሰልጠን ልምድ ሳይኖረው ረጅም አመት በአርሴን ዌንገር መንበር ስር የነበረውን አርሴናል ለመረከብ መቃረቡ አስገራሚ ሆኗል።

ቡድኑን ለመረከብ የተለያዩ አሰልጠኞች ታጭተው የነበሩ ቢሆንም በተለይ ማሲሚላኖ አሌግሪ ከጁቬንቱስ ጋር ለመቆየት መምረጣቸው ለአርቴታ መልካም እንደሆነለት ታውቋል።

የክለቡ አስተዳዳሪዎችም የወቅቱን የእግርኳስ ፍልስፍና መረዳት የሚችል ወጣት አሰልጣኝ መፈለጋቸው ደግሞ ሌላው አርቴታን ተመራጭ ያደረገው ሆኗል።

በዚህም ምክንያት አርቴታ የአርሴናል አሰልጣኝ ለመሆን በመርህ ደረጃ እንደተስማማ ታለላቅ የዜና አውታሮች ገልፀዋል።

አሰልጣኙ በቀጣዮቹ ቀናት ፊርማውን አስቀምጦ በይፋ የክለቡ አሰልጣኝ እንደሚሆን የሚጠበቅ ሲሆን የራሱ የሆነ የአሰልጣኞች ቡድንም እንደሚያዋቅር ተነግሯል።

ከዚህ የቡድን ስብስብ ውስጥም ሳንቲ ካዞርላ አንዱ እንደሚሆን መረጃዎች በስፋት እየገለፁ ይገኛሉ።

የአርቴታ ወደ አርሴናል ለማቅናት መቃረብ በደጋፊዎች የተዘበራቀ ስሜት ፈጥሯል።አንዳንዶቹ ልምድ ስለሌለው ስራው ሊከብደው እንደሚችል ሲጠቅሱ ሌሎቹ ደግሞ ከፔፕ ጓርዲዮላ ጋር መስራቱ እና ለፕሪምየርሊጉ እንግዳ ባለመሆኑ ድጋፋቸውን የሚሰጡ አልጠፉም።

የናንተስ አስተያየት?

Advertisements