በማንችስተር በተደረገው የጎዳና ላይ የ 10ሺ ሜ ውድድር ጥሩነሽ ዲባባ አሸነፈች

ዛሬ በማንችስተር የተካሄደው የታላቁ ማንችስተር የጎዳና ላይ የአትሌቲክስ ውድድር በሴቶች ጥሩነሽ ዲባባ ለአምስተኛ ጊዜ ስታሸንፍ ሞ ፋራህ በወንዶች ለመጀመሪያ ጊዜ አሸንፏል።

በየአመቱ በማንችስተር የሚካሄደው “የታላቁ ማንችስተር የአትሌቲክስ ውድድር” ዛሬ ተከናውኗል።

በወንዶች እና በሴቶች ዘርፍ በተካሄደው ውድድር በሴቶች ኢትዮጵያዊቷ ጥሩነሽ ዲባባ ስታሸንፍ በወንዶች ደግሞ እንግሊዛዊው ሞ ፋራህ አሸንፏል።

ጥሩነሽ አሸናፊ የሆነችበት ሰአት 31.08 በሆነ ሰአት በመግባት ሲሆን ጠንካራ ተፎካካሪዋ እንደምትሆን ተጠብቃ የነበረችው ኬኒያዊቷ ጄፒኮስጊ በ 31:57 በሁነ ሰአት በሁለተኛነት አጠናቃለች።

ጥሩነሽ የማንችስተር የጎዳና ላይ ውድድርን የዛሬውን ጨምሮ ለአምስተኛ ጊዜ ማሸነፍ ችላለች።አትሌቷ ከዚህ ቀደም 2013፣2014፣2016 እና 2017 ላይ አሸናፊ መሆኗ ይታወሳል።የዛሬው ድሏም ውድድሩን ለሶስተኛ ተከታታይ ጊዜ አሸናፊ እንድትሆን አድርጓታል።

በወንዶች ሞ ፋራህ ዩጋንዳዊውን ሞሰስ ኪፕሲሮን ቀድሞ ለመጀመሪያ ጊዜ የታላቁን ማንችስተር የአትሌቲክስ ውድድርን አሸንፏል።

ጠንካራ ፉክክር በተደረገበት የወንዶች ውድድር ሞ ፋራህ በመጨረሻ ፍጥነቱን ተጠቅሞ 28:27 በሆነ ሰአት ውድድሩን በአንደኝነት አጠናቋል።

Advertisements