ኤምሬ ቻን በቀጣይ ሳምንት ጁቬንቱስን እንደሚቀላቀል ይጠበቃል

ጀርመናዊው የሊቨርፑል አማካይ የሆነው ኤምሬ ቻን ከቻምፕየንስ ሊጉ የፍፃሜ ጨዋታ በኋላ ወደ ጁቬንቱሰ የሚያደርገው ዝውውር እውን እንደሚሆን ተነግሯል።

አማካዩ ከባየርሊቨርኩሰን በ 10 ሚሊየን ፓውንድ ከፈረመ በኋላ ከቀዮቹ ጋር ባለፉት አመታትን በአማካይ ስፍራ ላይ ሲጫወት ቆይቷል።

ጥሩ የኳስ ችሎታ ያለው ኤምሬ ቻን ከባለፈው መጋቢት ጀምሮ በጀርባ ጉዳት ለሊቨርፑል አስራ በአንድ ጨዋታዎች ላይ መሰለፍ አልቻለም።

ቻን የፊታችን ቅዳሜ ስድስተኛውን የቻምፕየንስ ሊግ ዋንጫን ለማግኘት ከማድሪድ ጋር የሚፋለው የሊቨርፑል ቡድን ውስጥ ቢገኝም የመሰለፍ እድል ያገኛል ተብሎ ግን አይጠበቅም።

ተጫዋቹ ሊቨርፑል ናቢ ኬታን ማስፈረሙ ተከትሎ በቀጣይ ከቡድኑ ጋር የመቀጠል እድሉ የጠበበ በመሆኑ ስሙ ከተለያዩ ክለቦች ጋር ሲያያዝ ቆይቷል።

በተለይ ከጣሊያኑ ጁቬንቱስ ጋር ስሙ በተደጋጋሚ ጊዜ ሲነሳ ከቆየ በኋላ በቀጣይ ሳምንት ሙሉ ለሙሉ የአሮጊቷ ተጫዋች መሆኑ እንደሚረጋገጥ ታውቋል።

የጁቬንቱስ ዳይሬክተር የሆኑት ጁሴፔ ሞራታም የሰጡት አስተያየትም ዝውውሩ ለመጠናቀቅ ቀናት ብቻ እንደቀሩት ፍንጭ የሰጠ ሆኗል።

ሞራታ ዝውውሩ ከቻምፕየንስ ሊጉ የፍፃሜ ጨዋታ በኋላ እንደሚጠናቀቅ እምነቱ እንዳላቸው ገልፀዋል።

ኤምሬ ቻን በሰኔ ወር ላይ ኮንትራቱ የሚጠናቀቅ በመሆኑ ወደ ጁቬንቱስ የሚያቀናው በነፃ ዝውውር ይሆናል።አዲሱ ደሞዙም በሳምንት 85ሺ ፓውንድ እንደሚሆን ተሰምቷል።

Advertisements