አርሰናል ከቀጣዩ ወር በኋላ ከሳንቲ ካዞርላ ጋር እንደሚለያይ አሳወቀ

​ከ 2012 ጀምሮ ከመድፈኞቹ ጋር ቆይታ የነበረው ስፔናዊው ሳንቲ ካዞርላ ኮንትራቱ በቀጣዩ ወር ከተጠናቀቀ በኋላ ከመድፈኞቹ ጋር በይፋ እንደሚላይ ይፋ ሆኗል።

ተጫዋቹ 33ኛ አመቱ ላይ የሚገኝ ሲሆን ባጋጠመው ጉዳት ምክንያት ከጥቅምት 2016 በኋላ ወደ ሜዳ መመለስ አልቻለም።

ነገርግን ከሰሞኑን ወደ ለንደን በመመለስ ልምምድ እንደጀመረ ተነግሮ የነበረ ሲሆን በአርሴን ዌንገር ሽኝት ላይም በኤምሬትስ መታየቱ ይታወሳል።

አርሰናል አርቴታን አዲሱ የክለቡ አሰልጣኝ ሆኖ ከተሾመ ካዞርላ የአሰልጣኞች ቡድን ውስጥ ሊካተት እንደሚችል ቢነገርም አሁን በተሰማ መረጃ መሰረት ግን ካዞርላ ወደ ቀድሞ ክለቡ ቪያሪያል ለመመለስ መቃረቡ ነው።

አርሰናልም ለክለቡ 180 ጨዋታዎችን ካደረገው ካርዞላ ጋር ያለውን ቆይታ የተጫዋቹ ኮንትራት በቀጣዩ ወር ከተጠናቀቀ በኋላ እንደሚለያይ አሳውቋል።

ተጫዋቹ “ከብዙ ጥሩ ቆይታዎች በኋላ አርሰናልን ስለምለቅ ተከፍቻለው።ከክለቡ ጋር የነበረኝ ቆይታ እወደዋለው።አብረን ያሳለፍናቸው እነዛ የማይረሱ ጊዜያትን ሁሌ አስታውሳቸዋለው።የ 2014 የ ኤፍ ኤ ካፕ ፍፃመፀ መቼም የምረሳው አይደለም።የዚህ ክለብ አባል ስለነበርኩ ኩራት ይሰማኛል።” ሲል ስሜቱን ተናግሯል።

ካዞርላ በአርሰናል ቆይታው ሁለት የኤፍ ኤ ካፕ ዋንጫን ማግኘት የቻለ ሲሆን ለክለቡም በአጠቃላይ 29 ጎሎችን ሲያስቆጥር 37 ኳሶችን ደግሞ ጎል እንዲሆኑ አመቻችቶ አቀብሏል።

Advertisements