ዶርትሙንድ ፌቭሬን በአሰልጠኝነት ቀጠረ

የጀርመኑ ክለብ ቦሩሲያ ዶርትሙንድ ሉሲየን ፌቭሬን የክለቡ አሰልጣኝ አድርጎ መቅጠሩን በይፋ አስታውቋል።

የፈረንሳዩ ሊግ 1 የውድድር ዘመን እንደተጠናቀቀ ከኒስ ክለብ የአሰልጠኝነት ኃላፊነታቸው የለቀቁት የ60 ዓመቱ አሰልጣኝ በሲግናል ኤዱና ፓርክ የሁለት ዓመት ኮንትራት ፈርመዋል።

“ቦሩሲያ ዶርትሙንድን ማሰልጠን ልቀበለው የምፋልግ በእጅጉ የሚማርክ ሚና ነው።” ሲሉ ፌቭሬ ለክለቡ ይፋዊ ድረገፅ ተናግረዋል።

“በእኔ ላይ እምነት ለማሳደር ኃላፊነት የወሰዱትን ላመሰግን እወዳለሁ። አሁን በአዲሱ ቡድን ውስጥ በጋር የምንሰራ ይሆናል።

“ቢቪቢ በአውሮፓ ካሉ ክለቦች ማራኪው ነው። በሚገባ ወደማውቀው እና በሁለት ዓመት የኒስ ቆይታዬ ከአዕምሮዬ ወዳልጠፋው ቡንደስሊጋው የመመለስ ፍላጎትም አለኝ።” ሲሉ አሰልጣኙ ጨምረው ተናግረዋል።

ፌቭሬ ከ2011 እስከ 2015 ድረስ ባሉት ጊዜያት ቦሩሲያ ሞንቼንግላድባኽን በማሰልጠን ለሁለት ጊዜያት ያህል ክለቡን ለሻምፒዮንስ ሊግ ውድድር ከማብቃታቸውም በተጨማሪ ሌላውን የጀመርን ክለብ ኸርታ በርሊንም ለሁለት ዓመታት አሰልጥነዋል።

ፌቭሬ ዶርትሙንድን የተረከቡት ለአምስት ወራት ክለቡን በመምራት ለሻምፒዮንስ ሊግ ውድድር በማብቃት ክለቡን የተሰናበቱትን ፒተር ስቶገርን በመተካት ነበር።

Advertisements