አርሰናል ኡናይ ኤምሬን በአሰልጣኝነት መቅጠሩን በይፋ ገለፀ

አርሰናል ኡናይ ኤምሬን በዋና አሰልጣኝነት መቅጠሩን በድረገፁ በይፋ ገልፅዋል።

የቀድሞው የፒኤስጂ እና ቫሌንሺያ አሰልጣኝ የለንደኑን ክለብ ከ22 ዓመታት ቆይታ በኋላ የውድድር ዘመኑ ሲጠናቀቅ የለቀቁትን አርሰን ቬንገር ምትክ በመሆን መረከብም ችለዋል።

የ46 ዓመቱ ስፔናዊ አሰልጣኝ ረቡዕ ረፋዱ ላይ በኤመራትስ ጋዜጣዊ መግለጫ አዳራሽ ተገኝተውም የአሰልጣኝነት ሹመቱን ይፋ አድርገዋል።

የክለቡ ከፍተኛ የድርሻ ባለቤት የሆኑት ስታን ክሮንኬ በክለቡ ይፋዊ ድረገፅ የኤምሬን የአሰልጣኝነት ሹመት አስመልክተው እንደገለፁት “ኡናይን ወደአርአናል እንኳን በደህና መጣህ ስንለው በደስታ ነው። እሱ የተረጋገጠለት አሸናፊ ነው። እሱ ለስራው ትክክለኛው ሰው በመሆኑ ላይ እና ለደጋፊዎቻችን፣ ለክለቡ ሰራተኞች እና የአርሰናል ፍላጎት ለሚመለከታቸው ሁሉ ዋንጫን እንደሚያስገኝ በራስ መተማመን አለን።” ብለዋል።

መድፈኞቹን ባአሰልጣኝነት የተረከበት ኡናይ ኤምሬም ሹመቱን አስመልክተው “[በእግርኳስ] በጨዋታ ታላቅ ከሆኑት አንዱ የሆነውን ክለብ በመቀላቀሌ ጥልቅ የደስታ ስሜት ተሰምቶኛል። አርሰናም በአጨዋወቱ፣ ለወጣቶች በሚስጠው ትኩረት፣ በድንቅ ስታዲየሙ፣ ክለቡ በሚጓዝባት መንገድ በመላው ዓለም የታወቀና የተወደደ ነው። በአርሰናል ታሪክ ላይ ወሳኝ አዲስ ምዕራፍ ለመጀመር ኃላፊነቱ የሚሰጠኝ በመሆኑ በጣም ተደስቻለሁ። ከስታን እና ጆሽ ክሮንኬ ጋር ተገናኝቻለሁ። እናም እነሱ በክለቡ ላይ ከፍ ያለ አዎንታዊ ተስፋ ያላቸው መሆኑ እና ለወደፊቱም ስኬትን ለማምጣት ቀርጠኛ መሆናቸው ግልፅ ነው። አብረን ልንሰራው በምንችለው እና አርሰናልን ለሚወዱ ሁሉ ልዩ ጊዜንና ትውስታን ለማበርከት ጉጉት አድሮብኛል።” በማለት ተናግረዋል።

ኡናይ አብዣኛውን ጊዜያቸውን በስፔኑ ሁለተኛ ዲቪዚዮን በመጫወት ካሳለፉ በኋላ የአሰልጣኝነት ዘመን ጅማሯቸውን በ2005 በሎር ዲፓርታቮ አድርገዋል። ሲቪያንና ፒኤስጂን ከመቀላቀላቸው በፊት አልሜሪያን፣ ቫሌንሻያ እና ስፓርታክ ሞስኮን በአሰልጣኝነት መርተዋል።

Advertisements