በእግርኳስ ተጫዋቾች ሁሉ የተወደደ እግርኳስ ተጫዋች፣ አንድሬስ ኢንየስታ

ባለፉት አስርት ዓመታት ሊዮኔል መሲና ክርስቲያኖ ሮናልዶን አንድሬስ ኢንየስታን የተዘነጋ ተጫዋች በማድረግ የእግርኳሱ ዓለም አበይት ርዕሰ ጉዳይ መሆን ችለዋል።

ይሁን እንጂ ዛሬ (ሃሙስ) ከባርሴሎና ጋር የነበረውን የረጅም ጊዜ የተጫዋችነት ዘመን በማጠናቀቅ ወደጃፓኑ ሊግ ክለብ ቪሴሎ ኮቤ ለመዛወር የሚያደርገውን ስምምናት ያጠናቃቀው ስፔናዊው ተዓምረኛ ተጫዋች የእግርኳስ ተጫዋቾች ሁሉ እግርኳስ ተጫዋች ነው።

የኢኒየስታ የጨዋታን ፍጥነት በማንበብ የሚኖረው የእግርኳስ ቴክኒክ፣ ዕይታ እና ችሎታ ከሱ ቀደም እንደተጫወተው እንግሊዛዊው ፓል ስኮልስ ሁሉ በስፓርቱ ዓለም ባሉ ዝነኛ ተጫዋቾች ዘንድ እውቅና እንዲያገኝ አስችሎታል።

እኛም የኢንየስታን ከፍ ያለ አስደናቂ ችሎታ በማወደስ በእሱ ላይ የግል አስተያየታቸውን የሰጡትን ዝነኛ የእግርኳስ ዓለም ሰዎችን አስተያየት ልናስቃኛችሁ ወደድን።

ፔፕ ጋርዲዮላ

“ኢንየስታ ፀጉሩን አያቀልምም፣ የጆሮ ጉትቻም አያደረግም እንዲሁም ምንም አይነት ንቅሳት የለበትም። ምናልባት ሚዲያውን እንዳይማርክ ያደረገው ያ ሳይሆን አይቀርም። ነገር ግን እሱ ምርጥ ነው።”

ሊዮኔል መሲ

“አንድሬስና እኔ ከተቃራኒዎቻችን ለመመሸሽ ስንል አካላችንን አብዝተን በመጠቀም እንመሳሰላለን። ነገር ግን እሱ እኔን የሚገርመኝ የሆነ ነገር አለው። ሁልጊዜም ልትይዘው እንደምትችል የምታስብበት ጊዜ አለ። ኳስ ከእሱ እንደምትነጥቀው ብታስብም ነገር ግን አትችልም። የተለየ ፍጥነት የለውም። ነገር ግን ሁልጊዜም ከአንተ የሚርቅበት የራሱ የሆነ ቴክኒካዊ ችሎታ አለው።

ፈርናንዶ ቶሬስ

“ኳስ ሲይዝ በዝግታ እንደሚታይ ካሜራ ሁሉም ነገር የሚቆም ይመስላል።”

ሮናልዲንሆ

“አሁን ሲጫወት ስመለለተው ዣቪን ያስታውሰኛል። እሱ [ኢንየስታ] ሁልጊዜም ጫፍ የደረሰ ብቃት ያለው ተጫዋች ነው። ከእኛ ጋር መጫወት ሲጀምር በጣም ወጣት ልጅ ነበር። ይህን ያህል ታሪክ እንዴት እንደሰራ መመልከት የሚገርም ነገር ነው።”

ሰርጂዮ ራሞስ

“ኢንየስታ ሁሉም እናቶች ለሴት ልጆቻቸው የወንድ ጓደኛ እንዲሆንላቸው የሚፍልጉት አይነት ሰው ነው። ቁጥሮች በእግርኳስ ህይወቱ ላይ ያደረጋቸውን ነገሮች ሁሉ ማወቅ እንድትችል ያደረጉሃል። በዓለም ላይ ከእሱ ጋር የሚነፀፀሩ ተጫዋቾች ጥቂት ናቸው።”

ዣቪ

“ያለምንም ጭቅጭቅ የተሟላ ብቃት ያለው ስፔናዊ ተጫዋች ነው። እሱ ሁሉ ነገር አለው። ከእሱ ጋር አብሮ መጫወት በጣም ቀላል ነገር ነው።”

ዴቪድ ሲልቫ

“ጋዜጦች ሁልጊዜም ከሮናልዶና ከመሲ መካከል ምርጡ ማን እንደሆነ ይጠይቁኛል። ነገር ግን ለእኔ አንድ ግልፅ ነገር አለ። ቁጥር አንዱ አንድሬስ ነው። በሜዳ ላይ አስቸጋሪ የሚባሉ ነገሮችን እንኳ ማድረግ ይችላል። ከኳስ ጋርም ምትሃተኛ ነው። እንዲሁም ተፅእኖ ፈጣሪ ነው።”

ቪሴንቴ ዴል ቦስኬ

“እሱ የተሟላ ተጫዋች ነው። ማጥቃትና መከላከል ይችላል። [የግብ ዕድል] ይፈጥራል፤ ያስቆጥራልም።”

ሴስክ ፋብሬጋዝ

“እሱ ፈጣሪ ተጫዋች ነው። ኳስን እየገፋ መሮጥ ይችላል። አስደናቂ የመጨረሻ የግብ ዕድል የምትሆን ኳስ ማሳለፍም ይችላል። ኳስን ማቀበል በቻለባቸው እያንዳንዱ ዓመታት ላይም እንደግብ ዕድል ፈጣሪነቱ ሁሉ ብዙ ግብ አስቆጣሪም ነበር። ለእኛ በራስ መተማመን ምንጭም እሱ ነው። በጨዋታዎች ላይ ኃላፊነቶችን በየጊዜው አብዝቶ ሲወስድ ልትመለከተው ትችላለህ። በማጥቃት እንቅስቃሴ ላይም የቡድኑ ማሳያ ተጫዋች ነው።”

Advertisements