ሮናልዶ ከ ሳላህ፡ የሻምፒዮንስ ሊጉ ፍፃሜ ቁልፉ ተጫዋቾች

ክርስቲያኖ ሮናልዶ እና ሞሐመድ ሳላህ ሪያል ማድሪድና ሊቨርፑል በሚያደረጉት የሻምፒዮንስ ሊግ ጨዋታ ቁልፍ ተጫዋቾች ስለመሆናቸው ቀጣዩ የስካይ ስፖርት ዘገባ ቁጥራዊ ትንታኔ ይዳስሳል

የ2018ቱ የሻምፒዮንስ ሊግ ፍፃሜ በጋራ ከ17 ላላነሱ ጊዜያት ውድድሩን ሻምፒዮን መሆን በቻሉ ክለቦች መካከል የሚደረግ ነው።

ሪያል ማድሪዶች በአምስት የውድድር ዘመናት ለአራተኛ ጊዜ ሊቨርፑል ደግሞ ውድድሩን ስድስት ጊዜ በማሸነፍ (ዋንጫውን ለ12 ጊዜያት ማንሳት ከቻሉት ሪያል ማድሪድ እንዲሁም ለሰባት ጊዜያት ሻምፒዮን መሆን ከቻሉት ኤሲ ሚላኖች ቀጥለው) ሶስተኛው ክለብ ለመሆን ይህን ጨዋታ የሚያደርጉም ይሆናል።

ይህ ጨዋታ በአውሮፓ አምስት አበይት ሊጎች ውስጥ ከሚጫወቱ ሶስት ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ ተጫዋቾች መካከል ሁለቱን እርስ በእርስ ያፋልማል። ሞሐመድ ሳላህና ክርስቲያኖ ሮናልዶ በየግላቸው 44 ግቦችን ማስቆጠር ችለዋል። በዚህ የውድድር ዘመን ሊዮኔል መሲ ብቻ ከእነሱ የተሻለ ግብ (45) አለው።

ሳላህ ለሊቨርፑል ካስቆጠራቸው ግቦች ሰማኒያ ሁለት በመቶውን ያስቆጠረው በግራ እግሩ ሲሆን፣ በአንፃሩ ከሮናልዶ የዚህ የውድድር ዘመን ግቦች 61 በመቶው የተገኙት በቀኝ እግር ከተቆጠሩ ግቦች ነበር።

ሳላህ ካደረጋቸው የግብ ሙከራዎች ኳስና መረብን በማገናኘት የተሻለ ንፅፅር አለው። ነገር ግን ያስቆጠራቸው ግቦች ግቦቹን ካስቆጠረባቸው ደቂቃዎች ጋር ሲነፃፀር የሮናልዶ ልቆ ይገኛል። ሆኖም ግብፃዊው በፍፁም ቅጣት ምት ያስቆጠረው አንድ ግብ ብቻ ሲሆን ፓርቱጋላዊ ተጫዋች ግን ካቆጠራቸው ግቦች ሰባቱን ያስቆጠረው በፍፁም ቅጣት ምት ነው።

በዚህ የውድድር ዘመን የሁለቱ ተጫዋቾች የአንገት ለእንገት ፉክክር በቁጥር
ሳላህ ሮናልዶ
44 ግቦች 44
51 ጨዋታ 43
36 በግራ እግር 10
6 በቀኝ እግር 27
2 በጭንቅላት 7
5 ከሳጥን ውጪ 2
1 ፍፁምቅጣትምት 7
23% ሙከራን ወደግብመለወጥ 16%
93 ግቦች በደቂቃ 81
14 ግብ ማመቻቸት 8
71 ግብ በደቂቃ ተሳትፎ 69
12 የጨዋታ ቀዳሚ ግብ 9

ሁለቱም ተጫዋቾች በዚህ የውድድር ዘመን ለክለባቸው ባደረጓቸው ጨዋታዎች የመጀመሪያውን ግብ ባስቆጠሩባቸው ጨዋታዋች ክለቦቻቸው ሽንፈት አልገጠማቸውም። ሊቨርፑል በ12 ጨዋታዎች ላይ ያልተሸነፈ ሲሆን፣ ከዚህም ዘጠኙን ሲያሸንፍ፣ በሶስቱ ደግሞ አቻ ተለያይቷል። ከእነዚህ መካከልም ሳላህ በሲቲ እና በሮማ ጨዋታዎች ላይ ያስቆጠታቸው ቀዳሚ ግቦች ይገኙበታል።

በተመሳሳዩ ሮናልዶ ለክለቡ የመጀመሪያ ግብ ማስቆጠር በቻለባቸው ጨዋታዎች ሪያል ማድሪድ ስምንቱን ሲያሸንፍ በአንዱ ብቻ አቻ በመለያየት ምንም ዓይነት ሽንፈት አልገጠመውም። ሮናልዶ በዚህ የውድድር ዘመን ተሰልፎ በተጫወተባቸው 14 የሻምፒዮንስ ሊጉ ጨዋታዎች 15 ግቦችን በመረብ ላይ በማሳረፍ ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ ሲሆን፣ ሳላህ እና የቡድን አጋሩ ፊርሚኖ ደግሞ እያንዳንዳቸው 10 ግቦችን በማስቆጠር በዝርዝሩ ላይ ተከታዩን ደረጃ ይዘው ተቀምጠዋል።

የአምስት ጊዜ የባሎን ዶር አሸናፊው ሮናልዶ አምስት የሻምፒዮንስ ሊግ ፍፃሜዎችን በማሸነፍ የመጀመሪያው ተጫዋች ለመሆን ይህን ጨዋታ የሚያደርግ ይሆናል። ባለፉት አራት የውድድር ዘመናት ላይም ከሪያል ማድሪድ ጋር ሶስት ጊዜ አሸናፊ መሆን ሲችል በ2007/08 ደግሞ ከማንችስተር ዩናይትድ ጋር ዋንጫውን መሳም ችሏል።

ከ1992 ወዲህ በአራት የሻምፒዮንስ ሊግ ፍፃሜ ጨዋታዎች ላይ ድል በመቀዳጀት የቻሉ ተጫዋቾች አንድሬስ ኢንየስታና ክላረንስ ሲዶርፍ ብቻ ናቸው። ሮናልዶ ከሁለት በላይ ግቦች ማስቆጠር የቻሉ ተጫዋቾች በሌሉበት በሻምፒዮንስ ሊጉ ፍፃሜ ባደረጋቸው አምስት የፍፃሜ ጨዋታዎች ላይ አራት ግቦችን ማስቆጠር ችሏል። እንዲሁም ተጫዋቹ በዛሬ ምሽቱ ጨዋታ ላይ መሰለፍ ከቻለ ለስድስት ጊዜያት ካህል በውድድሩ የፍፃሜ ጨዋታ ላይ መሰፍ ችሎ ከነበረው ፓውሎ ማልዲኒ ጋር የሚስተካከል ይሆናል።

የሮናልዶ የሻምፒዮንስ ሊግ የፍፃሜ ክብረወሰኖች
የውድድር ዘመን ተጋጣሚዎች ውጤት ግቦች
ሪያል ማድሪድ 2016/17 ጁቬንቱስ ድል 4-1 2
2015/16 አት.ማድሪድ አቻ 1-1, ድል 5-3 በፍ.ቅ.ም. 0
2013/14 አት.ማድሪድ ድል 4-1 በጭ.ሰዓት 1
ማን.ዩናይትድ 2008/09 ባርሴሎና ተሸነፈ 0-2 0
2007/08 ቼልሲ አቻ 1-1፣ ድል 6-5 በፍ.ቅ.ም. 1
ፍፃሜ ተጋጣሚዎች ውጤት ግቦች
2017 የፊፋ የዓለም ክለቦች ዋንጫ ግራሚዮ ድል 1-0 1
2017 ሻምፒዮንስ ሊግ ጁቬንቱስ ድል 4-1 2
2016 የፊፋ የዓለም ክለቦች ዋንጫ ካሺማ አንትሌርስ ድል 4-2 3
2016 የአውሮፓ ዋንጫ ፈረንሳይ ድል 1-0 0
2016 ሻምፒዮንስ ሊግ አት.ማድሪድ አቻ 1-1፣ ድል 5-3 በፍ.ቅ.ም. 0
2014 የፊፋ የዓለም ክለቦች ዋንጫ ሳን ሎሬንዞ ድል 2-0 0
2014 ሻምፒዮንስ ሊግ አት.ማድሪድ ድል 4-1 በጭ.ሰዓት 1

ሮናልዶ በዚህ የሻምፒዮንስ ሊጉ የውድድር ዘመን 46 ግቦችን በማስቆጠር ማጣሪያውን ጨምሮ በአንድ የውድድር ዘመን ብዙ ግብ በማስቆጠር ክብረወሰን መያዝ የቻለውን ሊቨርፑልን የሚገጥምም ይሆናል። ከእነዚህ የሊቨርፑል ግቦች መካከል 31 ግቦች የተቆጠሩት በሳላህ (11)፣ ፊርሚኖ (11) እና ሳዲዮ ማኔ (9) ነበር።

የ25 ዓመቱ ግብፃዊው ተጫዋች በሁሉም የዚህ የውድድር ጨዋታዎች 44 ግቦችን ማስቆጠር ችሏል። በዚህም በ2002/03 ይህን ያህል ግብ ማስቆጠር ችሎ ከነበረው የማንችስተር ዩናይትዱ ሻን ኒስል ሮይ ውጪ ማንም አይስተካከለውም። ይህ ብቻ ሳይሆን ሳላህ በ47 ግቦች በ1983/84 በኢያን ረሽ ተይዞ የነበረውን የሊቨርፑል ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪነት ክብረወሰን ለመስበር የቀረው ሶስት ግቦች ብቻ ነበር።

ለሳላህ ይህ ጨዋታ በክለብ እግርኳስ በአበይት የዋንጫ ፍፃሜ ላይ ሲጫወት የመጀመሪያው ይሆናል። በፍፃሜ ጨዋታዎች ላይ ግብ ለሃገሩ አንድ ጊዜ ተሰልፎ መጫወት የቻለ ሲሆን፣ በጋቦን በተካሄደው በዚህ የ2017ቱ የአፍሪካ ዋንጫ ፍፃሜ በካሜሮን የ2ለ1 ሽንፈት ደርሶበታል።

በአንፃሩ ግን ለሮናልዶ የዛሬ ምሽቱ የፍፃሜ ጨዋታ በአበይት የክለቦች ውድድር ዋንጫ ላይ 17ኛው የፍፃሜ ተሳትፎው ይሆናል። ፓርቱጋላዊ የፊት ተጫዋች በሚያስገርም ሁኔታ በተሰለፈባቸው 16 የፍፃሜ ጨዋታዎች 12ቱን ማሸነፍ ሲችል በአራቱ ብቻ ሽንፈት ገጥሞታል። በአጠቃላይ ተሰልፎ በተጫወተባቸው 18 የሃገሩና የክለብ አበይት የፍፃሜ ጨዋታዎች በ13ቱ ላይ ድል ቀንቶታል።

ሮናልዶ ባለፈው ሳምንት ሪያል ማድሪድ ከቪላሪያል ጋር 2ለ2 በተለያየበት ጨዋታ ያስቆጠረው ግብ ከአምስቱ አበይት የአውሮፓ ሊግ ተጫዋቾች በዚህ የውድድር ዘመን ለሃገሩና ለክለቡ 50 ግቦችን በማስቀጠር ይህን ያህል ግብ ማስቆጠር የቻለ የመጀመሪያ ተጫዋች መሆን አስችሎታል።

በሚደንቅ ሁኔታም ለሃገሩና ለክለቡ 50 እና ከዚያ በላይ ግቦችን በተከታታይ ማስቆጠር ሲችል ይህ ለስምንተኛ ጊዜው ነው።በተጨማሪም ለመጨረሻ ጊዜ ባደረጋቸው ያለፉት 19 ጨዋታዎች 28 ግቦችን በማስቆጠር ለሪያል ማድሪድ ተሰልፎ በተጫወተባቸው 437 ጨዋታዎች 460ኛ ግቡ ሆኖም ተመዝግበውለታል። ሳላህ ደግሞ ለሊቨርፑል ተሰልፎ በተጫዉባቸው ያለፉት 19 ጨዋታዎች 19 ግቦችን አስቆጥሯል።

ሁለቱ ተጫዋቾች ከሁለት ወራት በፊት በሮናልዶ በጭማሪ ሰዓት በጭንቅላት በተቆጠሩ ሁለት ግቦች ፓርቱጋል ግብፅን በዙሪክ 2ለ1 በረታችበት የወዳጅነት ጨዋታ ላይ እርስ በእርስ መገናኘት ችለው ነበር።

በክለብ ውድድሮች ላይ ሁለቱ ተጫዋቾች የተገናኙበት ብቸኛ ጨዋታ በ2016ቱ የሻምፒዮንስ ሊግ 16ቱ ክለቦች የሚሳተፉነት ዙር ላይ የሮናልዶው ሪያል ማድሪድ የሳላህን ሮማን በድምር ውጤት 4ለ0 የረታበት ጨዋታ ሲሆን፣ ከአራቱ ግቦች ሁለቱን ደግሞ ያስቆጠረው ሮናልዶ ነበር። ሳላህ ከዚህ ቀደም ሪያል ማድሪድን የገጠመበት ብቸኛው ጨዋታም ነበር።

ሮናልዶ ሊቨርፑልን ለመጨረሻ ጊዜ በገጠመበት አራት ጨዋታዎች ሶስት ግቦችን ማስቆጠር ቢችልም፣ ከዚያ ቀደም ቀዮቹን በገጠመበት የመጀመሪያ ሰባት ጨዋታዎች ላይ ግን ግብ ማስቆጠር ሳይችል ቆይቷል።

እነዚህ ሁሉ የግምት ውስጥ ገብተው የዓለማችን አስደናቂ ብቃት ያላቸው ሁለቱ ተጫዋቾች ፍልሚያ በዩክሬን ኪየቭ የሚደረገውን የዛሬ ምሽቱን ጨዋታ በጉጉት እንዲጠበቅ ያደርጉታል። ታዲያ ከውድድር ዘመኑ ምርጥ ተጫዋቾች በዚህ ጨዋታ ላይ ማን ጎልቶ ይታይ ይሆን?