ፖል ሜርሰን: ማድሪድ በሊቨርፑል ተሸንፎ ዚዳን በስራው ከቀጠለ እገረማለው

ማድሪድ እና ሊቨርፑል በሚያደርጉት የምሽቱ ጨዋታ ላይ አሸናፊው የአንፊልዱ ቡድን ከሆነ ዚዳን ከማድሪድ ሊሰናበት እንደሚችል የቀድሞ የአርሰናል ተጫዋች የሆነው ፖል ሜርሰን ተናግሯል።

ምሽት ላይ ተጠባቂው የቻምፕየንስ ሊግ የፍፃሜ ጨዋታ ሲደረግ ሪያል ማድሪድ ከሊቨርፑል የተሻለ አሸናፊ የመሆን ቅድሚያ ግምት ተሰጥቶት ነው።

ነገርግን የርገን ክሎፕ በፍፃሜ ጨዋታ እርግማናቸው ተገፎ አሸናፊ ከሆኑ በሊቨርፑል ስኬታማ አመታቸው የሚሆንላቸው ሲሆን በዚዳን የአመቱ ስኬት ላይ ደግሞ ቀዝቃዛ ውሀ ይቸልሱበታል።

የላሊጋውም ይሁን የንጉስ ዋንጫ በባርሴሎና የበላይነት በመጠናቀቁ ለማድሪዶች የቻምፕየንስ ሊጉ ዋንጫን ማንሳት ትርጓሜው ብዙ ነው።

ነገርግን ይህ ሳይሆን ድሉ ወደ ሊቨርፑል ካቀና የዚነዲን ዚዳን ከማድሪድ ጋር የሚኖረው ቆይታ አጠራጣሪ እንደሚሆን እየተነገረ ይገኛል።

የቀድሞ የአርሰናል ተጫዋች የነበረው ፖል ሜርሰንም ይህን ሀሳብ በሚገባ ተጋርቶታል።ቡድኑ በላሊጋው በባርሴሎና በሰፊ ነጥብ መቀደሙ የቻምፕየንስ ሊጉ ዋንጫ የማንሳት ግዴታ ውስጥ እንደገባ ያስታውሳል።

“በጥሎማለፍ ጨዋታዎች ስለ አሰልጣኞች አቅም መናገር ይከብዳል። ምክንያቱም ጥሎ ማለፍ ላይ ትንሽ እድል ያስፈልጋል፣ለማሸነፍም ጥሩ ድልድል ያስፈልገሀል።

“ዚዳን ሶስት ጊዜ በተከታታይ የቻምፕየንስ ሊጉን ዋንጫ ማሳካት ይችላል።ይህ ከሆነ ለሱ ትልቅ ስኬት ነው።ነገርግን ተሸንፎ በስራው ላይ ከቆየ እገረማለው ምክንያቱም እሱ በአመቱ ከባርሴሎና በብዙ ርቀት በነጥብ ተቀድሞ አጠናቋል።” ሲል ተናግሯል።

Advertisements