ይፋዊ: ሊቨርፑል ብራዚላዊውን ፋቢንሆን ማስፈረሙን አሳወቀ


ሊቨርፑል ብራዚላዊውን የሞናኮ አማካይ የሆነውን ፋቢንሆን ማስፈረሙን አሳውቋል።

ቀዮቹ ለዝውውሩ 43.7 ሚሊየን ፓውንድ እንዳወጡ የታወቀ ሲሆን ተጫዋቹም በፈረንጆቹ ሀምሌ 1 ላይ የህክምና ምርመራውን ካደረገ በኋላ በይፋ ዝውውሩን ያጠናቅቃል።

ስለ ዝውውሩ የተናገረው ፋቢንሆ “ይህ ዝውውር ሁልጊዜ የምፈልገው ነበር።ክለቡም በጣም ትልቅ ነው፣መሰረተ ልማቱም የተለየ ነው።

“የዚህ ያህል ትልቀት ያለው ክለብ ወደ እኔ መጥቶ ፍላጎቱን ሲያሳይ መልሼ ማሰብ አላስፈለገኝም።

“በክለቡ የራሴ የሆነ ታሪክ መፃፍ እሞክራለው።ከክለቡ ጋርም ዋንጫ ማንሳት እንደምችል ተስፋ አደርጋለው።የክለቡ የታሪክ አካል ሆኜም ለማደግ፣ለመማር እና እራሴን ለማሻሻል እሞክራለው።” ሲል ተናግሯል።

የ24 አመቱ ተጫዋች የፕሮፌሽናል ህይወቱን የጀመረው በሳኦፖሎ ፓውሊና በሚባል ክለብ ውስጥ ሲሆን በመቀጠል ለፉሉሚኔንሴ መጫወት ችሏል።

2012 ላይ ወደ ፖርቹጋል በማቅናት ለ ሪዮአቬ ከተጫወተ በኋላ በውሰት ወደ ሪያል ማድሪድ ማቅናት ችሏል።

በ አምስት አመታት ለፈረንሳዩ ሞናኮ መጫወት የቻለው ፋቢንሆ በ 225 ጨዋታዎች 29 ጎሎችን ማስቆጠር ችሏል።

ተጫዋቹ ወደ አንፊልድ ማቅናቱ ጀርመናዊው ኤምሬ ቻን ከክለቡ ጋር የመልቀቅ እድሉ የሰፋ ሆኗል።

ኤምሬ ቻን በነፃ ዝውውር ወደ ጁቬንቱስ ለመዘዋወር እጅግ መቃረቡን የአሮጊቷ ዳይሬክተር ጨምሮ መናገራቸው ይታወሳል።

Advertisements