ፕላቲኒ ወደእግርኳሱ ዓለም የመመለስ ፍላጎት አላቸው

የቀድሞው የአውሮፓ እግርኳስ ማህበር ፕሬዝዳንት ሚሼል ፕላቲኒ የስዊዘርላንድ የፌዴራል አቃቤ ህግ ካልተገባ የፋይናንስ ወንጀል ክስ ነፃ ያዳረቸው መሆኑን ተከትሎ ወደእግርኳሱ ዓለም ለመመለስ አቅደዋል።

የቀድሞው የአውሮፓ እግርኳስ ማህበር አመራር አካል ዋና ባለስልጣን ሴፕ ብላተርን ተክተው የዓለም አቀፉን የእግርኳስ አመራር ለመምራት ባዝግጅት ላይ ሳሉ በ2015 ታህሳስ ወር በፊፋ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ከኃላፊነታቸው እንዲነሱ ተደረገው ነበር። ፊፋ በ2011 በብላተር ማረጋገጫ ከአስር ዓመት በፊት ለፈፀሙት ስራ ለፕላቲኒ 1.87 ሚሊዮን ዩሮ ክፍያ ፈፅመዋል በሚል ሁለቱንም ኃላፊዎች ከኃላፊነታቸው አንስቶ ነበር።

ፈረንሳያዊው ታሪካዊ እግርኳስ ተጫዋች፣ ፕላቲኒ በፕላተር ላይ በተከፈተው ክስ “ምስክር እና ተከሳሽ” በመሆን ፍርድ ቤት ቀርበው ነበር። ይሁን እንጂ በፕላቲኒ ስም የቀረበባቸው ምንም አይነት ክስ አልነበረም።

የስዊዝ አቃቤያን ህግ የተከፋላቸውን ክፍያ አስመልክቶ ምርመራ ሲያደርግ ቢቆይም ባለፈው አርብ ዕለት ግን ፕላቲኒ ነፃ መሆናቸውን መግለፁን የፈረንሳዩ ጋዜጣ ለ ሞንድ ዘግቧል። የስዊዘርላንድ የህዝብ አቃቤያን ህግ ቢሮ ምንም እንኳ “እስካሁን” በፕላቲኒ ላይ ክስ እንዲመሰርት የሚያስችል ማስርጃ ባይገኝም ምርመራው ግን “ጨርሶ ያለመጠናቀቁን” ቅደሜ ዕለት ገልፅዋል።

የአቃቤ ህግ ቃል አቀባይ ለፈረንሳዩ የዜና ምንጭ አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ እንደገለፁት በጉዳዩ ላይ አዲስ ማስረጃ ከተገኘ ፕላቲኒ ፍርድ ቤት እንዲቀርብ ሊጠየቅ ይችላል።

ጉዳዩን አስመልክተው ለአሶሼትድ ፕሬስ የዜና ምንጭ የተናገሩት ፕላቲኒ ደግሞ ዜናው “በቤተሰቤ እና ለእኔ ቅርብ በሆኑ ሰዎች ላይ ለረጅም ጊዜ የዘለቀውን መሸማቀቅ እንዲያበቃ የሚያደረግ” ነው ሲሉ ገልፀው። “እመለሳለሁ ወዴት፣ መቼና እንዴት? ስለሚለው አሁን መናገር ባልችልም። ወደእግርኳስ ግን እመለሳለሁ። ምክኒያቱም እግርኳስ ህይወቴ ነው። ይህንን ነገር የሚነጥቀኝን ማንንም ደግሞ አለበቀበልም።” ሲሉ አክለው ተናግረዋል።

የፊፋ የቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ ፕላቲኒ ከዓለም እግርኳስ እንዲታገዱ ጥሎት የነበረውን የአስር ዓመታት እግድ ወደስድስት ዓመት ዝቅ አድርጎታል። ፕላቲኒ ምንም እንኳ የኋላ ኋላ በስፓርት የግልግል ፍርድ ቤት የተጠለባቸው የስድስት ዓመት ዕግድ ወደአራት ዓመት ዝቅ ቢልላቸውም፣ ግንቦት 2016 የፈረንሳይ እግርኳስ ታላቁ ሰው በተጣለባቸው ዕግድ ምክኒያት በመጨረሻ ያቀረቡት የእጩነት ጥያቄ ውድቅ በመሆኑ ከአውሮፓ እግርኳስ ማህበር የፕሬዝዳንትነት ኃላፊነታቸው በገዛ ፈቃዳቸው ለቀዋል።

የ62 ዓመቱ ሰው ኃምሌ 2017 ላይ ቅጣቱ የበዛ ነው በሚል ለስዌዝ የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሌላ ይግባኝ ጥያቄ ቢያቀርቡም ፍርድ ቤቱ ይግባኙን ውድቅ አድርጎታል። ይህን ተከትሎም የቀድሞው የጁቬንቱስ ተጫዋች እስከጥቅምት 2019 ድረስ የተጣለባቸው ዕድቅ ተፈፃሚ እየሆነባቸው ይገኛል።

“ፊፋ የተጣለብኝን ቅጣት ለማንሳት ድፍረትና እና መልካም ሃሳብ ይኖረዋል ብይ ተስፋ አደርጋለሁ።” ሲሉም ፕላቲኒ ለአጃንስ ፍራንስ ፕሬስ ተናግረዋል።

Advertisements