“አባቴ የእኔን [የእግርኳስ ስራ] ህይወት አስመልክቶ ውሳኔ አያሳልፍም። ስለዚያ የምወስነው እኔ ነኝ።” – ኔይማር

ብራዚላዊው የፒኤስጂ ኮከብ ኔይማር አባቱን አወድሶ ነገር ግን በእግርኳስ ህይወቱ የወደፊት ዕጣ ፈንታውን የሚወስነው በራሱ እንደሆነ ገልፅዋል።

ኔይማር የዓለም የዝውውር ክብረወሰን በሆነ 222 ሚ.ዩሮ ዋጋ ከባርሶሎና ወደፓሪሱ ክለብ ፒኤስጂ ከተዛወረ በኋላ ለክለቡ መጫወት የቻለው ገና ለአንድ የውድድር ዘመን ብቻ ቢሆንም ስሙ ግን ከሪያል ማድሪድ ዝውውር ጋር ተያይዞ ይገኛል።

የ26 ዓመቱ የፊት ተጫዋች አባት ለረጅም ጊዜያት ያህል የተጫዋቹ አማካሪና ወኪል ሆኖ ቢያገለግልም ነገር ግን ተጫዋቹ ማንኛውንም የእግርኳስ ህይወቱን አስመልክቶ ውሳኔ የሚያሳልፈው በግሉ እንደሆነ ተናግሯል።

“አባቴ የእኔን [የእግርኳስ ስራ] ህይወት አስመልክቶ ውሳኔ አያሳልፍም። ስለዚያ የምወስነው እኔ ነኝ።” ሲል ብራዚላዊው ተጫዋች ለቪያአይፒ መፅሄት ተናግሯል።

“እሱ ማንኛውንም ጥያቄ የማቀርብለት ምርጥ አማካሪ ነው። ነግር ግን የመጨረሻው ውሳኔ የእኔ ነው።

“አባቴ ከእግርኳስ እኩል የሚጨነቅባታቸው ሌሎች ጉዳዮች አሉት። ስለዚህ የእኔ ስራ ትኩረት የራሴ ብቻ ነው።”

ኔይማር በጉዳት እስካጠናቀቀበት የፒኤስጂ የመጀመሪያ የውድድር ዘመን ቆይታው ለክለቡ 28 ግቦችን መረብ ላይ ማሳረፍ ችሏል።

ተጫዋቹ ብራዚል በምድብ ኢ ስዊዘርላንድን፣ ኮስታሪካን እና ሰርቢያን ለምትገጥምበት የሩሲያው ዓለም ዋንጫ ራሱን እያዘጋጀም ይገኛል።

Advertisements