አስገራሚ : ዜነዲን ዚዳንን ለመቅጠር አስገራሚ ደሞዝ እንደቀረበለት ተሰማ

ከማድሪድ ጋር በድንገት የተለያየው ዜነዲን ዚዳን ከማድሪድ ደሞዙ በ አምስት እጥፍ የላቀ በቀን 120 ሺ ፖውንድ፣በወር 44 ሚሊየን ፓውንድ የሚያስገኝለት ስራ እንደቀረበለት ተሰምቷል።

ሶስት የቻምፕየንስ ሊግን ዋንጫ በማንሳት ታሪክ የሰራው ዜነዲን ዚዳን ከማድሪድ ጋር በራሱ ፈቃድ መለያየቱ ይታወሳል።

ከድንገታዊ ውሳኔው አንድ ቀን በኋላ የተሰማው ዜና ግን ምናልባትም አሰልጣኙ ውሳኔውን ያሳለፈው ምራቅ የሚያስውጥ ሌላ ስራ ስላገኘ እንደሆነ የዛሬ መረጃዎች ያመለክታሉ።

የ 2022 የአለም ዋንጫ የምታዘጋጀው ኳታር በውድድሩ ላይ በቀጥታ አላፊ በመሆኗ ከወዲሁ ትኩረት ሰጥታ እየተንቀሳቀሰች ትገኛለች።

ለውድድሩም ከወዲሁ ጠንካራ ቡድን ለመገንባት ጠንካራ አሰልጣኝ ለመቅጠር ያሰበች ሲሆን ምርጫዋም ዚዳን ላይ ማድረጓ ታውቋል።

ኳታር ብሔራዊ ቡድኗን እንዲያሰለጥን ለዚዳን ያቀረበችው ደሞዝ ደግሞ በቀን 120 ሺ ፓውንድ ወይንም በአመት 44 ሚ ፓውንድ አካባቢ ሲሆን ይኸው ክፍያ ከግብር ነፃ መሆኑ አስገራሚ ሆኗል።

ይህ ደግሞ በማድሪድ ከግብር ጋር በአመት 8 ሚሊየን ፓውንድ ለሚያገኘው ዚዳን ለውጡ ከ አምስት እጥፍ በላይ እንደሆነ መመልከት ይቻላል።

ይህ ደግሞ አሰልጣኙ እንዳሰበው ሳይሆን በፍጥነት ወደ ስራው ሊመለስ እንደሚችል እየተነገረ ይገኛል።

Advertisements