መሲ እስራኤልን የሚገጥም ከሆነ ደጋፊዎች ማሊያውን ሊያቃጥሉት ይገባል – የፍልጤም እግርኳስ ፌዴሬሽን ኃላፊ

አርጄንቲናዊው ኮከብ ሊዮኔል መሲ እስራኤልን በወዳጅነት ጨዋታ የሚገጥም ከሆነ ደጋፊዎች ፎቶውን እና መለያውን ማቀጠል እንደሚገባቸው የፍልስጤም እግርኳስ ፌዴሬሽን ዋና ኃላፊ ጂብሪል ራጁብ ተናግረዋል።

የጆርጌ ሳምፓውሌ ቡድን የዓለም ዋንጫው ከመጀመሩ በፊት በሚያደርገው የመጨረሻ የወዳጅነት ጨዋታው የፊታችን ቅዳሜ እስራኤልን ለመግጠም ዕቅድ ይዟል።

ነገር ግን ራጆብ ጨዋታውን ለፓለቲካ ማሳሪያ ትጠቀምበታለች በሚል በፊፋ የሃገራት ደረጃ በ98ኛ ላይ የምትገኘውን እስራኤልን ወቅሰዋል።

እናም ብዙዎችን በሚያስማማ መልኩ የዓለማችን ምርጡ ተጫዋች መሲ በዚህ ጨዋታ ላይ የሚጫወት ከሆነ ደጋፊዎች የባርሴሎናውን ኮከብ ዒላማቸው ውስጥ እንዲያስገቡት ነግረዋል።

“እሱ ትልቅ ተምሳሌት ነው። ስለዚህ እሱን በግል ዒላማ እናደርገዋለን። እናም ሁሉም ምስሉን እና መለያውን እንዲያቃጥሉ እንዲሁም እንዲንቁት እንጠይቃለን።” ሲሉ እሁድ ዕለት ለጋዜጠኞች ተናግረዋል።

የፍልስጤም እግርኳስ ፌዴሬሽን ዋና ኃላፊ ጂብሪል ራጁብ

“እኛም መሲ ይመጣል ብለን ተስፋ አናደርግም።” ሲሉም ፕሬዝዳንቱ ጨምረው ተናግረዋል።

አርጄንቲና ከእስራኤል ጋር የምታደረገው ይህ የወዳጅነት ጨዋታ በዓለም ዋንጫው ውድድር አይስላንድን ከምትገጥምበት ጨዋታ አንድ ሳምንት ቀደም ብሎ የሚደረግ ነው።

Advertisements