ሳንቲ ካዛሮላ ቪላሪያልን ተቀላቀለ

ሳንቲ ካዛሮላ አርሰናልን ለቆ ከዚህ ቀደም የተጫወተበትን የላ ሊጋውን ክለብ ዳግመኛ መቀላቀሉን ቪላሪያል በይፋዊ ድረገፁ ገልፅዋል።

የ33 ዓመቱ ሳንቲ ካዛሮላ በመሃል ለሪክሬቲቮ ሁልቫ ለአንድ ዓመት ያህል ከመጫወቱ ውጪ በ2011 ለማላጋ ከመፈረሙ በፊት ባሉት የመጀመሪዎቹ የተጫዋችነት ዓመታት ለቪላሪያል ተጫውቶ አሳልፏል።

ካዛሮላ ዳግመኛ በሎስ ቦኩዌሮኖቹ ለአንድ ዓመት ከተጫዋተ በኋላ 123 ጨዋታዎችን መጫወት የቻለበትን አርሰናልን ተቀላቅሏል።

ካዛሮላ በመጀመሪያ መድፈኞቹን ሲቀላቀል በአጥቂ አማካኝነት ሚና የነበረ ቢሆንም በኋላ ግን ወደመኃል አማካኝነት ሚና ተዛውሯል።

ካዛሮላ በ2016 ጥር ወር ላይ በገጠመው የተረከዝ ጉዳት በአርሰናል የነበረውን የመጨረሻዎቹ የተጫዋችነት ዘመናት መጥፎ አድርገውበታል።

ቪላሪያልም ተጫዋቹ በአዲሱ የውድድር ዘመን በቡድኑ ውስጥ መልካም ጊዜን እንደሚያሳልፍ ተስፋ በማድረግ ለቅደመ የውድድር ዘመን ክለቡን መቀላቀሉን በይፋ ገልፅዋል።

Advertisements